የጠ/ቤተ ክህነቱ ሠራተኞች “የዳኛ ያለህ! ለቤተ ክርስቲያኒቱ ዳኝነት ይታይላት” የሚል ጽሑፍ ለቅዱስ ሲኖዶስ አባላት አሰራጩ

ከአማናዊቷ ደጀ ሰላም የተወሰደ!! አቡነ ጳውሎስ ሃይማኖትን በመበረዝ እና በሕገ ቤተ ክርስቲያን ጥሰት መጠየቅ እና መወገድ ነበረባቸው:: ሊቃነ ጳጳሳቱ “ሰማዕታት፣ ነውረኞች፣ ዘገምተኞች እና ጥቅመኞች” በሚል በአራት ተከፍለዋል:: አቡነ ጳውሎስ የቅዱስ ሲኖዶስን ሕግ እና ውሳኔ እየሻሩ የቅዱስ ሲኖዶስን ጉባኤ መምራታቸው ሊያሳፍራቸው … Continue reading

More Galleries | Leave a comment

በማኅበረ ቅዱሳን የአሜሪካ ማዕከል “ ብጹዕ አቡነ ፋኑኤል ” ከሰሜን አሜሪካ ሀገረ ስብከት እንዲነሱ ቅዱስ ሲኖዶስን ጠየቀ፡፡

ማዕከሉ በድረ ገጹ ባስነበበው አቋም ገላጭ ደብባቤው አቡነ ፋኑኤል ከቤተክርስቲያን ዓላማ በተቃራኒው መቆማቸውን በማብራራት፣ እሳቸው ተነስተው ደግ አባት ይመደብ ዘንድ ጠይቋል፡፡ ለዚህም ጥያቄውም አብነት የሚሆኑትን ማሳያዎች በዝርዝር አቅርቧል፡፡ በተለይ በሰሜን አሜሪካ ቤተ ክርስቲያን ህጋዊ እውቅና ከሰጠቻቸው ማኅበራት ጋር ለመስራት ፈቃደኛ … Continue reading

More Galleries | Leave a comment

ሰበር ዜና :- የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ዋና ሓላፊ ከሓላፊነታቸው ተነሡ!!

ከአማናዊቷ ደጀ ሰላም!! የዋና ሓላፊው መነሣት በቤተ ክህነቱ የጨለማ ቡድን የተቀነባበረ ነው፤ የአቡነ ጳውሎስ ስውር ትእዛዝና የአቡነ ገሪማ የተለመደ አድርባይነት እንዳለበትም ተረጋግጧል የመምሪያው ሊቀ ጳጳስ “እኔ በማላውቅበት ኹኔታ የመምሪያው ሓላፊ ሊቀየሩ አይችሉም” በማለት ርምጃውን ተቃውመዋል “ተግባሩ በቤተ ክህነታችን እየኾነ ያለው … Continue reading

More Galleries | Leave a comment

እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!!!

This gallery contains 1 photo.

More Galleries | Leave a comment

ከአሰቦት ገዳም የመጡ መነኮሳት አቤቱታ አቀረቡ!!!

ፍትሕ ጋዜጣ መጋቢት 28 2004 ዓ.ም በቅርቡ የመቃጠል አደጋ የደረሰበት በምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ሚኤሶ ወረዳ ከሚገኘው አሰቦት ገዳም የመጡ ስምንት አባቶች ‹‹ገዳሙ ይከለልልን ሠራዊት ተመድቦ ይጠበቅልን›› ሲሉ ለጠቅላይ ቤተ ክህነት እና ለመንግስት አቤቱታ አቀረቡ፡፡ አቤቱታውን ለማሰማት ከገዳሙ የመጡት የሃማኖት … Continue reading

More Galleries | Leave a comment

ይድረስ ለአባ ጳውሎስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ፣ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም፣ ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት፣ የዓለም ሃይማኖቶች ምክር ቤት ለሰላም የክብር ፕሬዝዳንት

This gallery contains 1 photo.

  አባታችን ይህቺን ትንሽዬ ጦማር እከትብሎ ዘንድ ያነሳሳኝ “ሰሞኑን” በተከሰቱ ሁለት ዓበይት ጉዳዮች ዙሪያ ጥያቄዎች ስላሉኝ ጥያቄ ለመጠየቅና በጉዳዮቹ ዙሪያ የተሰማኝንና የታዘብኩትን ነገር ልነግሮት በመፈለጌ ነው:: ይህቺን ጦማር ስከትብሎ እርሶ ጋር ላይደርስ ይችላል የሚል ጥርጣሬና ሀሳብ አላደረብኝም:: እናም በአንድም ሆነ … Continue reading

More Galleries | 1 Comment

ዲ/ን ዳንኤል ክብረት ይቅርታ ጠየቀ

(ዕንቁ መጽሔት ቅጽ 4 ቁጥር 48 2003 ዓ.ም ሙሉ ጽሑፉን ያገኙታል) • የማኅበሩ የስራ አመራር ጉባኤ ውሳኔ የኔም ውሳኔ ነው እጋራዋለሁ • አንድ ነገር ለበጎ ተሰርቶ ያልታሰበ አደጋ አምጥቷል • እኔ ጽሑፉን ሳዘጋጅ ማኅበራችን ማኅበረ ቅዱሳን ከገጠመው ፈተና እንዲወጣ የተሻለ … Continue reading

More Galleries | 5 Comments

ብፁዕ አቡነ ሚካኤል አረፉ

This gallery contains 2 photos.

የሰሜን ምዕራብ ትግራይ ሽሬ እንዳ ሥላሴ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ሚካኤል ዛሬ ነሐሴ 9 ቀን 2003 ዓ.ም. አረፉ፡፡ ብፁዕነታቸው ማክሰኞ ነሐሴ 3 ቀን በቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ቅዳሴ ቀድሰው እንደነበር ቤተሰቦቻቸው የገለጹ ሲሆን በቅዱስ ገብርኤል ሆስፒታል የሐሞት … Continue reading

More Galleries | 3 Comments

ዲ/ን ዳንኤል ክብረት ‘’የዓለም የሰላም አምባሳደር’’ የሚል ማዕረግ ተሰጠው

(ምንጭ፡-አዲስ ዘመን ነሐሴ 12 ቀን 2003ዓ.ም. 70ኛ ዓመት ቁጥር 342)
ቪዥን ኢትዮጵያ ፎረ ዲሞክራሲ የተባለ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት መልካም ዜጋን በመቅረጽ እና የመልካም አስተዳደር ተግባራትን በማጠናከር ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርገዋል ያላቸውን አራት ግለሰቦች ሊቀ ዲሞክራት እና ስድስት ግለሰቦችን ‘’የዓለም የሰላም አምባሳደር’’ የሚል ማዕረግ ሰጥቷል፣ በዚህም የነገረ ቤተክርስቲያን ተመራማሪ እና ደራሲ የሆነው ዲ/ን ዳንኤል ክብረት ‘’የዓለም የሰላም አምባሳደር’’ የሚል ማዕረግ ሰጥቶቷል፡፡ ስነስርዐቱ ላይ በመገኘት ማዕረጉን የሰጡት ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ ሲሆኑ የፌደራል ጉዳዮች ሚንስትር ዶ/ር ሽፈራው ተክለማርያም ‘’የዓለም የሰላም አምባሳደር’’ የሚል ማዕረግ ካገኙት ግለሰቦች አንዱ ናቸው፡፡ ቪዥን ኢትዮጵያ ፎረ ዲሞክራሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ታደለ ደርሰህ በስነስርዐቱ ላይ እንደገለጹት የተመረጡት ግለሰቦች በግልና በመንግስታዊ ተቋማት የላቀ ሥራ የሰሩ ናቸው፡፡ የዜጎች መብት እንዲታወቅ ና እንዲከበር ከፍ ያሉ ተግባራት አከናውነዋል አርአያና ምሳሌ ሆነው የሚጠቀሱም ናቸው ድርጅታችን ወደፊትም እንዲህ ያሉ ግለሰቦችንና ኃላፊዎችን ለተግባራቸው ዕውቅና በመስጠት የመሸለም ሥራ እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡ ለአገልግሎት ባሕር ማዶ የሚገኘው ዲ/ን ዳንኤል ክብረትም በባለቤቱ አማካኝነት የማዕረግ ስጦታውን ተቀብሏል፡፡

Posted in ዜና | 10 Comments

የእኔን ጣሉኝ ያለኽ…

በከና ከሸማ ተራ   ዮናስ ወደ መርከቧ የውስጠኛ ክፍል ዘልቆ ተኝቷል፡፡ መደበቁ ነበር፡፡ ከሰው ቢሆን ጥሩ ነው ሊያዛልቅ ስለሚችል ፡፡ ዮናስ ግን ቀልድ ጀምሯል፡፡ ከእግዚአብሔር ለመደበቅ በማሰብ የጀመረውን የእብድ አሳብ ተግብሮት ተኝቷል፡፡ መርከቧ በማእበሉ መናወጥ ጀመረች፡፡ከመርከቧ ባለሟሎች እስከ ተሳፋሪዎቿ ድረስ … Continue reading

More Galleries | 6 Comments

የብፁዕ አቡነ ሚካኤል አጭር የሕይወት ታሪክ

ብፁዕ አቡነ ሚካኤል በትግራይ ክልል በሰሜን ምዕራብ ዞን በአስገደ ፅምብላ በደብረ ዓባይ ገዳም አካባ በሰጋሉ አጥቢያ/ገበሬ ማኅበር/ከአባታቸው ከአለቃ ዓባይ ወ/ገብርኤልና ከእናታቸው ከወ/ሮ ታደለች ንጉሤ በ1942 ዓ.ም ተወለዱ፡፡ ዕድሜያቸው ለትምህርት እንደ ደረሰ በዚሁ በታላቁ በደብረ ዓባይ ገዳም የድጓና የአቋቋም መምህራን ከነበሩት … Continue reading

More Galleries | 1 Comment

መንግሥተ ሰማያት ገብቼ ተመለስኩ!

የወንደምስሻ አየለ (ቀሲስ-ኢንጂነር) ወቅታዊ የፊስ ቡክ መልእክት አንባቢያን ቢያዩት ይጠቅማል ብለን ስላሰብን አውጥተነዋል ሳናስፈቅድ በማውጣታችን ቀሲስ-ኢንጂነር ወንድምስሻን ይቅርታ እንጠይቃለን!         ዕለቱ እሑድ ነሐሴ ፰ ከጠዋቱ ፭ ሰዓት ነው። የቤተክርስቲያን የፍልሰታው የመጨረሻ ሰንበት የአምልኮ ሥርዓት ተፈጽሞ ብዙው ወደ ቤቱ ገብቷል፤ በቤተክርስቲያን … Continue reading

More Galleries | 9 Comments

አባ ሙሴ ጸሊም ኢትዮጵያዊ

 አባ ሙሴ ጸሊም በትውልዱ ኢትዮጵያዊ ሲሆን አስቀድሞ በውንብድና ኑሮ ሕይወቱን ይገፋ ነበር፡፡ ሰዎች ከገድሉ የተነሳ ያደንቁታል፡፡እርሱ አስቀድሞ መንግሥተ ሰማያትን ገፍቷት ነበርና እርሱ በሥጋው ጠንካራ ፤ በሥራውም ኃይለኛ ነበር፡፡ አባ ሙሴ ጸሊምም ፀሐይን ለሚያመልኩ ሰዎች አገልጋይ ነበረ ፤ ብዙ ጊዜም ወደ … Continue reading

More Galleries | 2 Comments

ሢመተ ጵጵስናን የማቀራመት ጽኑ መግፍኢ

በባሮክ ዘሣልሣይ ሺሕ (ከዚህ ቀደም በግንቦት ወር 2003 ዓ.ም. አውራምባ ታይምስ ጋዜጣ ላይ የወጣ፡፡) የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ከቅብጥ (Coptic) ቤተ ክርስቲያን ጥገኝነት እንድትላቀቅ ለማድረግና አገራዊ ጳጳሳትን ለማፍራት ብዙ አድካሚ ትግል ተካሒዷል፡፡ ለዚህም ሃይማኖታዊ ብሔርተኞች ያላሰለሰ ጥረት አድርገዋል፡፡ ለዘመናት የተካሔደው የሃይማኖት … Continue reading

More Galleries | 10 Comments

እምነት እና እውቀት እንዲህ ያደርጋል

ምንጭ ሎሚ መጽሔት ቅ ጽ 1 ቁጥር 2ነሐሴ 2003ዓ.ም. ከግዛው ታዬ አንዳንድ አጋጣሚዎች እውነተኛ ጀግኖችን ያረጋግጡልናል አንዳንድ ክስተቶች ደግሞ ሳናውቀው በመሃይሞች እጅ ላይ እንዳለን ይጠቁሙናል ሁሉም ቢሆን እውነት እና ንጋት እያደር ይጠራል በማለት የመኖር ግደታን የሚያስቀምጡብን ተሳስተዋል ለማለት ቢከብድም በዚህ … Continue reading

More Galleries | 6 Comments

የዜና ቤተ ክርስቲያን ልዩ ዕትም ርእሰ አንቀጽ ሲኖዶስ አይወግንም

ከደጀ ሰላም የጡመራ መድረክ (ዜና ቤተ ክርስቲያን፤ 56ኛ ዓመት ቁጥር 121፤ ነሐሴ 2003 ዓ.ም/ PDF)፦ በአሁኑ ጊዜ የጠቅላላው ኅብረተሰብ የየዕለቱ የመነጋገሪያ አጀንዳና ጊዜ ማሳለፊያ ከሆኑት ነገሮች ዋና ዋናዎቹ ሦስት ነገሮች ናቸው፡፡ እነዚህም ሦስት ነገሮች የእግር ኳስ ጨዋታ፣ ገመና ድራማ እና … Continue reading

More Galleries | 2 Comments

የማኅበረ ቅዱሳን አመራሮች ከብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ጋር ውይይት አደረጉ

እሁድ ነሐሴ 15 ቀን 2003ዓ.ም ከሰዓት በኋላ የማኅበረ ቅዱሳን አመራሮች ከብጹዕ ወቅዱስ አብነ ጳውሎስ ጋር ውይይት እንዳደረጉ የአገር ውስጥ ምንጮች የገለጹ ሲሆን ወቅታዊ በሆነው የተሃድሶ እንቅስቃሴ፣ አባ ሠረቀ ብርሐን ጉዳይ እና ሌሎች ግለሰቦችን በተመለከተ የውይይት አጀንዳ መሆኑም ተነግሯል፡፡ ይህ ውይይት … Continue reading

More Galleries | 24 Comments

ሃይማኖትና ፖለቲካ በኢትዮጵያ፡ የትውልድ ክፍተትና ግጭት ከኢ/ኦ/ተ/ቤ አንፃር

የተከበራችሁ የገብር ኄር የጡመራ ሰሌዳ አንባብያን አብዩ በለው ጌታሁን የተባሉ ግለሰብ ወቅታዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ የላኩልንን ጽሑፍ ክፍል አንድ እንደሚከተለው አቅርበነዋል፡፡ በአብዩ በለው ጌታሁን (abiyuye@gmail.com) ኦገስት 2011, ከኮሎምበስ, ኦሃዮ ክፍል አንድ እንደ መነሻ ሃሳብና ማስገንዘቢያ 1ኛ. በአቶ በፍቅር ለይኩን (አቶ?) … Continue reading

More Galleries | Leave a comment

ሰበር ዜና -የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ መደበኛ ስብሰባ ዛሬ ይደረጋል

የአቡነ አብርሃም እና የአቡነ ኤዎስጣቴዎስ ከቦታቸው መነሳት ዋነኛ አጀንዳ ነው

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ መደበኛ ስብሰባ በዛሬው ዕለት ረቡዕ ነሐሴ 18 ቀን 2003 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ እንደሚያካሂድ ተገለጸ፡፡ ከስብሰባውም አጀንዳዎች ዋነኛው በዋሽንግተን እና አካባቢው ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም እና የሎስ አንጀለስ ና አካባቢው ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤዎስጣቴዎስን ጉዳይ ይሆናል፡፡ ከቅርብ ጊዜ በፊት በቀንደኛ የተሐድሶ አራማጅነታቸው የሚታወቁትን ሊቀ ስዩማን ኃይለጊዮርጊስ “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የሰሜን አሜሪካ ልዩ ሹም” በማለት በቅዱስ ፓትርያሪኩ መሾማቸው ሲሆን ውሳኔውን እና ሹመቱን በመቃወም ሁለቱም ሊቃነ ጳጳሳት የተቃውሞ ድብዳቤ መጻፋቸው ነው፡፡ የተቃውሞው ይዘት ቃለ አዋዲው እና ቀኖና ቤተክርስቲያን ተጥሷል የሚል ሲሆን በአንድ ሀገረ ስብከት የሁሉም የበላይ ሊቀ ጳጳሱ መሆን ሲገባው ከሊቀ ጳጳሱ በላይ “ልዩ ሹም” መሾም ተገቢ አይደለም ይላሉ፡፡ በዚህ ተቃውሞም የተነሳ ዛሬ በሚደረገው የቋሚ ሲኖዶስ አስቸኳይ ስብሰባ ሁለቱንም ሊቃነ ጳጳሳት ከቦታቸው በማንሳት ወደ አገር ቤት አንዲሄዱ ሊወሰን እንደሚችል ለቤተ ክህነቱ ቅርብ የሆኑ የገብር ኄር የጡመራ ሰሌዳ ምንጮች ገልጸዋል፡፡

Posted in ዜና | 7 Comments

ህገ ወጥነት በቤተ ክህነት ተባብሷል

This gallery contains 1 photo.

በሸዊት ገ/ኪዳን     shewitgbrkdn95@gmail.com      † የአዲስ አበባ ሰንበት ትምህርት ቤቶችን በቀል ይጠብቃቸዋል † አቡነ ዮሴፍ ሀገረ ስብከታቸውን በግፍ ተቀሙ † በጋሻው የተሃድሶ የለም ዘመቻውን ቀጥሎበታል † በመቐለ ተሃድሶ የለም የሚለውን ሪፖርት አቡነ ቀውስጦስ ተቃወሙት   † አባ … Continue reading

More Galleries | 15 Comments

የእኔን ጣሉኝ ያለህ -ክፍል ሁለት

ከገብርኄር
ባለፈው ጊዜ እጅግ በጣም የምናመሰግናቸው ፀሐፊ በከና ከሸማ ተራ ልከውልን ከፊሉን ባስነበብናችሁ “የእኔን ጣሉኝ ያለህ!” ጽሑፍ መግቢያ ተንተርሳችሁ አስተያየታችሁን የለገሳችሁንንና ቀጣዩን ጽሑፍ በጉጉት ስትጠባበቁ የነበራችሁ ውድ የገብር ኄር የጡመራ ሰሌዳ እንድምተኞች በሙሉ በቅድሚያ ስለተሳትፎአችሁ ከልብ እያመሰገንን ቀጣዩንና የመጨረሻውን ክፍል እነሆ ብለናል ሌሎቻችሁም ተሳታፊዎች በተመሳሳይ ሐሳባችሁን እንድትገልጹልን እየጠየቅን መልካም ንባብ እንዲሆንላችሁ እንመኛለን፡፡

 

በከና ከሸማ ተራ

መርከብ ቤተክርስቲያናችን ባህር በተባለች በዚህች ምድር እስካለች ደረስ/ አስታውሱ ቤተክርስቲያን ስንል ሦስት ወገን ሲኖራት አንዱን የክርስቲያኖች አንድነትን ማለቴ ነው/ ማዕበልና ወጀቡ ከወዲህ ወዲያ እንደሚንጣት እርግጥ ነው፡፡
በአገራችን ኢትዮጵያ በ1997 ዓ.ም ተከስቶ የነበረው የምርጫ ትርምስ የዕድል ቁጥር እንደሆነለት የሚታወቀው በጋሻው ደሳለኝ የመስቀሉ ሥር ቁማርተኞች በሚለው ቅጂ መጽሐፉ ከመርከቢቱ/ከቤተክርስቲያናችን/ ካፒቴን/ርዕስ/ እስከ ተሳፋሪዎቹ/ምዕመናን/ ይልቁንም ወንጌል ሲሰበክ የሚያንቀላፉ ሳንቲም ሲንቃጭል የሚነቁ በማለት ካህናቱን በአደባባይ ዘለፈና መርከቢቱ ስትናጥ እሱ ግን ወደ ውስጠኛው ክፍል ገብቶ ተኛ ዝነኛው፣ ቅባቱ የበዛለት፣ ወዘተ… እየተባለ በየዓውደምህረቱ ተንጎራደደ ይባስ ብሎ “ማኅበረ ቅዱሳን ወንጌል በሚሰበክበት ዓውደምህረት ወንጀል ሰብኮ ዓውደ ጦርነት ዓውደ ብጥብጥ አደረገው፡፡” አለ ያን ጊዜ በድሬዳዋ ማዕከሉ ይመስለኛል ማኅበረ ቅዱሳን ክስ መስርቶ በጋሻውን ፍርድ ቤት አቆመው መርከቧ መናወጧን ቀጥላላች ማንም ግን “እኔን ጣሉኝ” አላለም፡፡
ይባስ ብሎ መምህር ዘመድኩን “አርማጌዶንን” ይፋ አደረገ ይሄኔ የመርከቧ መናወጥ ባሰ በመጀመሪያ አርማጌዶን ለማን እንደሆነ በይፋ ባይገለጥም ከወዲያ ማዶ እነበጋሻው እኛን ነው ብለው እጅ ሰጡ “እኔን ጣሉኝ” ይላሉ ብለን ስንጠብቅ ጭራሽ በመምህር ዘመድኩን ላይ “አርፈህ ልጆችህን ብታሳድግ ይሻልሃል?” ከሚለው ዛቻ ጀምሮ ብዙ የሚሰቀጥጡ አፍ እላፊዎች በስልክና በአካል ይተላለፉ ጀመር፡፡ የመርከቧ መናወጥ ጨመረ የአራት ኪሎዎቹ ጋዜጦችና መጽሔቶችም ቤተክርስቲያናችንን የእንጀራቸው መብያ ሹካ ማድረጉን በሰፊው ተያያዙት፡፡ የመርከቧ ተሳፋሪዎች/ምዕመናን/ ተጨነቁ ኧረ እባካችሁ ይህንን ነገር ተውት ቢሉም የሚሰማቸው ጠፋ፡፡ ተንቀራፎ ተንቀራፎ ከወደ ጠቅላይ ቤተክህነት ስብከተ ወንጌል ክፍል ሊቀጳጳሱ ቢሮ ለመምህር ዘመድኩን የትፈለጋለህ መልዕክት ደረሰው፡፡ የመርከቢቱ ተሳፋሪዎች ጎሽ አንተም ተው አንተም ተው የሚል ተገኘ ብለን ተደስትን የሚገርመው ግን “አንተን ማን ፈቀደልህና ነው በቤተክርስቲያን ውስጥ ችግር አለ?” ብለህ የምታውጀው ሲሉ አቡኑ ዘመድኩንን ወቀሱት…..ትንሽ ቆየና ሌላ ማዕበል ደግሞ ተጨመረ የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ኃላፊ አባ ሠረቀ ብርሃን ወልደሳሙኤል ተነሱና ማኅበረ ቅዱሳንን በአደባባይ መክሰስና መውቀስ ጀመሩ ማኅበረ ቅዱሳንም መደበኛ ተግባሩን ነገር ቸል ብሎ ከኚሁ ሰው ጋር እሰጥ አገባ ገጠመ፡፡ መርከቧ መናጧ በረታ አባ ሠረቀብርሃንም ማኅበረ ቅዱሳንም በመርከቧ የውስጠኛ ክፍል ተኝተዋል፡፡ አንዲት ወ/ሮ እጅጋየሁ በየነ የምትባል ሴት /አንዳንዶች ኤልዛቤልም ይሏታል የነቢያት አሳዳጇን/ ተነሳችና የቅዱስ ሲኖዶስ አጀንዳ ሆነች፡፡ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ግቢ እንዳትደርስ ሲነገራት “የሲኖዶስ ውሳኔ ብሎ ነገር አላውቅም እኔን ግቢም አትግቢም የሚሉኝ አባቴ አቡነ ጳውሎስ ብቻ ናቸው” ብላ በአደባባይ በቅዱስ ሲኖዶስ ወሳኔ ላይ ተሳለቀች ይባስ ብላም የአቡነ ጳውሎስ ቋሚ ጠበቃ የቁም ሐውልት አሰሪ ሆነች እጅጋየሁ ያኔ ጳጳሳት አባቶቻችን በጨለማው ቡድን ሲደበደቡ መሪ ተዋናይ እንደነበረች መረጃዎች ፍንትው አድርገው ቢያሳዩም እሷ ግን ዓይኔን ግንባር ያድርገው አለች፡፡ ያው ከጨለማው ቡድን ጋር ወደ መርከቡ የውስጠኛ ክፍል ገብታ ለጥ ብላላች መርከቧ ግን አሁንም ትናጣለች፡፡የቅርቡን ላንሳና ጽሑፌን ልግታ ሦስት ዓይነት ዋና ዋና ማዕበላት፡-
የተሐድሶ እንቅስቃሴ ከድርጅት ወደ ድርጅቶች፣ከግለሰብ ወደ ማኅበር፣ ከኅቡዕነት ወደ ግልጽነት፣ ከመፍራት ወደ ድፍረት፣ከአንድ ከተማ ወደ ሀገር አቀፍ፣ ከጓዳ ወደ ብዙኃን መገናኛ፣ ከውጭ ወደ ውስጥ መዋቅራችን ዘልቆና ተጠናክሮ ቤተክርስቲያንን እየገዘገዘ ባላበት በዚህ አስራ አንደኛ ሰዓት በእነወ/ሮ እጅጋየሁና ግብራበሮቿ ተረቆ የቀረበና በቅዱስ ፓትርያርኩ የተፈረመበት ደብዳቤ “ተሐድሶ የሚባል የለም” ሲል ሰማነው አንድ ፓትርያርክ ልጆቼ እንዲህ ዓይነት ነገር ይወራል አጣርተን እስክናሳውቃችሁ ድረስ ቤተክርስቲያናችሁን በጥንቃቄ ጠብቁ ብሎ የአባትነቱን ይወጣል እንጂ የተያዘን የነብርን ጅራት ልቀቁ ብሎ ያውጃል? ቢሆንም ቤተክርስቲያኗን የተሐድሶ ማዕበል እየናጣት ነው ሁሉም ወደ ውስጠኛው ክፍል ገብቶ በምቾት ተኝቷል እንጂ የምዕመኑን “የልንጠፋ ነው” ጩኸት ሰምቶ እኔን ጣሉኝ የሚል የለም፡፡
ሁለተኛው ጉዳይ በቅርቡ ብሶት የወለዳቸው መንፈሳዊ ጀግኖች የአዋሳ ምዕመናን ባሰራጩትና ፀሐይ በሞቀው አገር ባወቀው ጉዳይ በበጋሻው ወጥ ረገጥ ንግግር ላይ መጽሐፍ ቢጤ የጻፉትን መምህር ዘመድኩንን እና ዲያቆን ደስታን በጋሻው እንደከሰሳቸው ሰማሁ ወሬውንም ተከሳሶቹ አረጋገጡልኝ ክሱም “ከምዕመኑ ልብ ውስጥ እንድወጣ አድርገውኛል” የሚል ነበር፡፡ በአንድ ወቅት ትንሽ የዝሆን ጆሮ ከሚዘንበው ሃይለኛ ዝናብ ተጠለለችበትና ዝናቡ ቆሞ ፀሐይ ብልጭ ስትል ትንኟ ከዝሆኑ ጆሮ ወጣች የዝሆኑን ውለታ አስታውሳ ልታመሰግነው ፈለገችና በጭንቅላቱ ዙሪያ የምስጋና በረራ አደረገች ዝሆኑ በረራው ስላልተሰማማው “ምን አድርግ ትይኛለሽ?” ሲላት “ዝናቡን በጆሮዎ ስላሳለፍኩ ላመስግንዎ ብዬ ነው” አለችው፡፡ ዝሆኑም “እባክሽ ጥፊልኝ እኔ ስትገቢም ሆነ ስትወጪም አላውቅም” አላት ይባላል፡፡ ዮናስስ አርፎ ነው የተኛው በጋሻው እና መሰሎቹ ግን ይንፈራገጣሉ፡፡ መርከቧ ግን ትናወጣለች፡፡ ሦስተኛውና የመጨረሻው ጉዳዬ የማኅበረ ቅዱሳን የውስጥ ጉዳይ ነው እግዚአብሔር ይመስገንና አያያዙ ከበድ ያለ ነበር፡፡የት ይደርሳል ያሉት ጥጃ ልኳንዳ ቤት ተገኘ እንዲባል ማኅበረ ቅዱሳን እራሱን በራሱ ሊበላልት ተነስቶ ነበር፡፡ ግን ቢላዋው ደነዘ እሰይ እንኳንም ደነዘ፡፡ በዚህ ጉዳይ ብዙ የማትተው አይኖረኝም ወንድሜን ዲ/ን ዳንኤል ክብረትን በግል ማኅበረ ቅዱሳንን ደግሞ እንደተቋም ላመሰግናቸው እወዳለሁ ዲ/ን ዳንኤል ክብረት ራሱ ይቅርታ ብሎ ባስነበበን ጽሑፍ ያውም በውስጣዊ/ኅሊና/ አብራክ ተንበርክኮ ይቅርታ መጠየቁ ለእኔ የእኔን ጣሉኝ ያለህ ጥያቄ ምላሽ ሰጥቶኛል፡፡ ዲ/ን ዳንኤል ክብረት በእውነት እኔን ጣሉኝ ነው ያልከው በዚህም ብዙ መሰዋዕትነት የከፈልክበትን ማኅበርህንና በማኅበርህ ቤተክርስቲያንህን ሊፈጠር ከሚችለው ተጨማሪ ማዕበል አትርፈሃል፡፡
እኔ ጽሑፌን ልቋጭ መርከቧን ማዕበሉ ክፉኛ እያናወጣት ነው የመርከቧ አለቆችም ሆኑ ተሳፋሪዎቿ ግን ያገኙት መላ የለም፡፡ በጋሻው እጅጋየሁ አባሠረቀ፣ ጌታቸው ዶኒ፣ አሰግድ፣ በሪሁን፣ ትዝታው ከጳጳሳቱም የምናውቃቸው ከማኅበረ ቅዱሳንም የምናውቃቸው ብቻ ሁሉም ተኝቷል የእኔን ጣሉኝ ያለህ!!!

Posted in ሐተታ | Leave a comment

“መምህር” ግርማ ታገዱ

“ዲቁና እንጂ ቅስና የለኝም በማለታቸው ታግደዋል” ሊቀ ጳጳስ አባ ቀውስጦስ
“ማስረጃ በማቅረቤ እግዱ ተነስቶልኛል” መምህር ግርማ
ከቅዳሜ ነሐሴ21ቀን2003 አዲስ አድማስ ጋዜጣ የተወሰደ
ሰላም ገረመው

ከሥርአት ውጭ በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች በርካታ ሰዎችን ጸበል አጠምቃለሁ እያሉ ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ ቤት ገዝተዋል የሚል ቅሬታ የቀረበባቸው መ/ር ግርማ ወንድሙ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የታገዱ ሲሆን በየጊዜው የሚሰነዘርባቸው ወቀሳና አሉባልታ እንደሆነና እግዱ እንደተነሳላቸው ተናግረዋል፡፡ “የአንድ ነጥብ አምስት ሚሊዮን ብር የመኖሪያ ቤትና ፒካፕ መኪና ያገኘሁት በሥጦታ ተገዝቶልኝ ነው” ብለዋል መ/ር ግርማ፡፡ ከመቁጠሪያ ጀምረ ቪሲዲ፣ጋዜጣና መጽሔት ጭምር የመምህር ግርማ ነው እየተባለ በየቤተክርስቲያኑ ሲሽጥ አይተናል የሚሊ ቅሬታ አቅራቢዎች በቤተክርስቲያን ብቻ ሳይሆን በቤታቸውም ፀበል አጠምቃለሁ እያሉ ከምዕመናን ብር ይሰበስባሉ በማለት ይተቻሉ፡፡ከሥርዓት ውጭ በሆነ መንገድ በሚሰበስቡት ብር የአንድ ነጥብ አምስት ሚሊዮን ብር ቤት ፒካፕ መኪና ሚኒባሶችና ሌሎች ንብረቶችን አካብተዋል ይላሉ ቅሬታ አቅራቢዎች። በደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከትየ 12 (አስራ ሁለት) ሰንበት ትምህርት ቤቶች ባቀረቡት ቅሬታ መምህር ግርማ የሚያካሂዱት የማጥመቅ ሥራ ሥርዓት የጣሰ ስለሆነ ሊያቆሙ ይገባል ብለዋል፡፡ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ረዳትና የሰሜን ሸዋ ሰላሌ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ አባ ቀውስጦስ “መ/ር ግርማ ላይ እገዳ የጣለው ቅስና የሌለው ሰው ማጥመቅ ስለማይችል ነው” ብለዋል፡፡ በዲቁና የሚያገለግል ሰው ይላላካል እንጂ አያጠምቅም የሚሉት አባ ቀውስጦስ “በአቶ ግርማ ላይ ቅሬታ ስለቀረበ ጠርተን ስናናግራቸው ዲቁና እንጂ ቅስና የለኝም በማለታቸው ሊታገዱ ችለዋል” ብለዋል፡፡ መምህር ግርማ በበኩላቸው እኔ ቅስናዬን ደብቄ ነው እንደዚያ ያልኩት ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡  “ጥያቄ የቀረበልኝ በቁጣ በመሆኑ ቅስና የለኝም ብዬ ተናግሬአለሁ” የሚሉት መምህር ግርማ “አሁን ማስረጃ በማቅረቤ እግዱ ተነስቶልኛል ይላሉ፡፡” አቡነ ቀውስጦስ ግን እግዱ አልተነሳም ብለዋል፡፡ አቶ ግርማ እግዱ ከተወሰነባቸው በኋላ ቅስና ስላለኝ እግዴ ይነሳልኝ የሚል ጥያቄ አቅርበው ነበር የሚሉት አቡነ ቀውስጦስ እኛ ሀሜትና ወሬን በመከተል ሳይሆን በህጋዊ መንገድ ጠይቀን የደረስንበት ውሳኔ ነው ብለዋል፡፡ በመ/ር ግርማ ንብረት ላይ ስለሚሰነዘረው ቅሬታ ተጠይቀው ስለሌላው ጉዳያቸው እኛ አያገባንም ብለዋል አቡነ ቀውስጦስ መ/ር ግርማ በበኩላቸው ከዚህ በፊትም መተተኛ ነው አስማተኛ ነው የሚል አሉባልታ እየተወራብኝ ነበር ያአልሳካ ሲላቸው ቅስና የለውም ተብያለሁ ይላሉ፡፡ አሁንም በሥራ ላይ መሆናቸውን በመጥቀስ ምንም በአሉባልታ ከምወደው ምዕመናን አይለየንም የሚሉት መ/ር ግርማ ንብረታቸውን በተመለከተ በሰጡት መልስ የውጭ ተመራማሪና ጆርጅ ቡሽ አማካሪ የነበሩ ግለሰብ ሲፈወሱ በአንድ ነጥብ አምስት ሚሊዮን ብር ቤትና ፒካፕ መኪና ተገዛልኝ ይሄ ስጦታዬ ነው ወሬኞች ግን ካቻማሊና ሚኒባስ አለው ብለው ያስወራሉ ብለዋል፡፡

Posted in ዜና | 18 Comments

“እመቤታችን” እና “ራዕይ”

በያሬድ ይስማሸዋ (yismayared21@gmail.com) ነገሩን ከሰማሁ ሦስት ዓመት ያልፈዋል እንደዋዛ ከነገረኝ ወዳጄ ጋር አጭር ክርክር ቢጤ አደረግንና ቋጨን ከዚህ በኋላ በድጋሚ አንስተን አልተወያየንበትም በኔ ቤት ጉዳዩ በዚያው ተቋጭቷል፣ ነገር ግን ጉዳዩ ቀላል አለመሆኑንና ስር የሰደደ ነገር መሆኑን የሰሞኑ ሁኔታዎች ስላሳዩኝ የመወያያ … Continue reading

More Galleries | 4 Comments

‹ቤተክርስትያኒቷ ትዘጋ›› የሚል ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ

                                                                              በፍቅር ሀለፎም fkrhalefom95@gmail.com
                                                                              ከአንድ አድርገን እና  ተዋህዶ ዛሬም ላይ የተወሰደ
 
 
 የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ፆመ ፍልሰታ ወቅት ሲሆን በቤተክርስትያናችን ህግና ስርዓት መሰረት ይህ ጊዜ ዲያቆናት ፤ ካህናት መነኮሳት ፤ ጳጳሳት እና ምእመናን ለሐዋርያት የተገለፅሽላቸው እናታችን ለእኛም በምህረት አትለይን እያሉ በፆም ፤ በፀሎት ፤ በስግደት የሚለምኑበት ጊዜ ቦታው በሐረር መንገድ አዋሽ ሰባትን አልፈው ካለው የጉምሩክ የፍተሻ ጣቢያ ትንሽ ኪሎ ሜትር አለፍ ብሎ ከአሰቦት ገዳም መገንጠያ ሳይደርስ ከዋናው አስፋልት አንድ ኪሎ ሜትር ላይ የሚገኝ የአባታችን የአቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ቤተክርስትያን
ሲሆን የቦታው ስም ቦርደዴ በመባል ይታወቃል፡፡ ይህ ቤተክርስትያን የሚገኝበት ቦታ ላይ ከ30 የማይበልጡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኞች ሲገኙ በቁጥር ከ40 እና ከ50 እጥፍ ልቀው የሚገኙት ግን ሙስሊም ማህበረሰቦች ናቸው፡፡ ይህ ቦታ  ከችግር ተላቆ አያውቅም፡፡ ቦታው  ድረስ ሄጄ በተመለከትኩበት ጊዜ እዚህ ቦታ ላይ ያለው የሙቀት መጠን ክረምት ሳይል በጋ ከ40 ድግሪ በላይ ስለሆነ ቆሞ ማስቀደስ እንደ እግዚሐብሔር መልካም ፍቃድ ፤ ምህረት ፤ ቸርነት እንጂ እንደ እኛ ብርታትና ጥንካሬ እንዳልሆነ ተረድቻለሁ፡፡
ቤተክርስትያኒቷ አካባቢ ያሉት ምዕመና ጧፍ ፤ እጣን ፤ ዘቢብ እና ንዋየ ቅዱሳትን ማሟላት አቅሙ ስለሌላቸው ይህ ችግር የቀን ተቀን የውስጥ ችግር ችግራቸው ሆኖ አሁንም አሉ ፡፡ የባሰ አታምጣ ነውና  አንድ ጊዜ ቅዳሴ ላይ ወንጌል ለማንበብ ጧፍ አልቆ በኩራዝ የተጠቀሙበት ጊዜም ነበር ፡፡
በአካባቢው የሚገኙ ከአክራሪ ወገን የሚመደቡት የእስልምና ተከታዮች በአካባቢው ላይ ለ24 ሰዓት ያህል ከ4 በሚበልጡ መስኪዶቻቸውን ድምፅ ማውጫ Speaker ወደ ቤተክርስትያን አዙረው ‹‹አላህ ዋክበር›› በሚሉበት ሁኔታ ላይ ምንም ጥያቄ ያላቀረቡት በአካባቢው የሚገኙ  ክርስትያኖች በዓመት አንድ ጊዜ ለ16 ቀናት ብቻ ያለውን የሱባኤ ጊዜ ለሊት ሰዓታት እና ኪዳኑ ፤ ጠዋት ትርጓሜው እና ስብከቱ ፤ ከሰዓት ቅዳሴው ረበሸን ብለው ቤተክርስትያኒቷ እንድትዘጋላቸው  ለአካባቢያቸው ወረዳ አስተዳደር ሰላማዊ ሰልፍ አድርገው መጠየቃቸውን አረጋግጠናል፡፡ ይህን ጥያቄ የመስተዳድሩ  ሃላፊ ከሰማ በኋላ ለሚቀጥለው ቀን የቀጠራቸው ሲሆን በሚቀጥለው ቀን ሲመጡ ምንም ምላሽ ስላላገኙ ሓላፊውን በኃይል ከቢሮ ያባረሩት ሲሆን ፡፡ ይህ ጥያቄያቸው የክልሉ መንግስ ጋር እንደደረሰ ፤ አካባቢው ላይ የሚገኙ ክርስትያኖች ጉዳዩን ወደ ፊደራል መንግስት የወሰዱት ሲሆን መንግስት የዛኑ ቀን ማታ አካባቢው ላይ የሚገኙ ፌደራል ፖሊሶች ማታ 3፡00 አካባቢ ወደ አካባቢው በፓትሮል በመምጣት ይህን ጥያቄ የጠየቁትን ሰዎች ግማሽ ያህሉን ለቅመው ወስደው ወደ እስር ቤት የከተቷቸው  ሲሆን የተቀሩትን ግን ሸሽተው አምልጠዋል፡፡ መንግስት ይህን እርምጃ ከወሰደ በኋላ ሁኔታውን በጥቂቱ ያረጋጋ ሲሆን ፡፡ በአሁኑ ወቅት አካባቢው በፊደራል ፖሊስ  እየተጠበቀ ይገኛል::
እኛ በአሁኑ ሰዓት እንትና 18 ገፅ ወቀሳ ፃፈ ፤ ያኛው ሰባኪ አውደ ምህረት ላይ እንዳይቆም ተከለከለ ፤ በዚህ መፅሄት ላይ እንትና መልስ ሰጠ ፤ አንዱ ይቅርታ አለ ሌላኛው ይቅርታ ተቀበለ እያልን ስራ መስራት በሚገባን ወቅት ወሬ ስናራግብ ለቤተክርስትያን መሆን በሚገባን ሰዓት ጊዜያችንን እና አቅማችንን አልባሌ ቦታ ላይ በማዋልና ትርፍ የሌለው ስራ በመስት ላይ እንገኛለን፡፡
አሁንም ጊዜው አልረፈደም ስለ ጥቂት ሰዎች ማውራታችንን አቁመን ስለ ቅድስት ቤተክርስትያን ዘብ እንቁም ዛሬ በሰላማዊ ሰልፍ ይህን የጠየቁ ሰዎች ነገ ምን ማድረግ እንደሚያስቡ ለማስረዳት መምህር ሊያሻን አይገባም፡፡
በዚች ምድር ላይ የምንቆየው እንደ ማቱሳላ 969 ዓመት አለመሆኑን አውቀን በኖርንበት፤በምንኖርበት  ጊዜ ሁሉ ከቤተክርስትያን ጎን ለመቆም ያብቃል፡
‹‹እግዚሐብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ
Posted in ዜና | 10 Comments

በአባ ጳውሎስ 20ኛ ዓመት በዓለ ሲመት 5 ሚሊዮን ብር ለማትረፍ ታቅዶል፡፡

 በሸዊት ገብረ ኪዳን (shewitgbrkdn95@gmail.com)
  • በአሉን ምክንያት በማድረግ 5 ሚሊዮን ብር ለማትረፍ ታስቧል
  • የአዲስ አበእና ጠንካራ ሀገረ ስብከቶች ጠቀም ያለ ገንዘብ ይጠበቅባቸዋል
  • ከተሳካና አውሮፕላኑከተገዛ አባ ጳውሎስ በአፍሪካ የመጀመሪያው ይሆናሉ
  • የጳጳሳት ሹመት ኮሚቴ ተቋቁሟል


 
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን 5ኛው ፓትርያርክ ሲሆኑ በ2004 ዓ.ም. ዘመነ ፕትርክናቸው 20 ዓመት ይሆነዋል በመሆኑም 20ኛው በዓለ ሲመት በደመቀ ሁኔታ እንዲከበር እና በዓሉን ምክንያት

ወ/ሮ እጅጋየሁ በየነ

በማድረግ ከሚሰበሰበው ገንዘብ ላይ 5,000000 (አምሰት ሚሊዮን) ብር እነወ/ሮ እጅጋየሁ ለግላቸው ለማትረፍ ያቀዱ ሲሆን ገንዘቡን ለመሰብሰብ ምክንያቱ የአውሮፕላን ግዢው እንዲሆን ና ከየአጥቢያው እና አቅም ካላቸው ሀገረ ስብከቶች ገንዘብ በማሰባሰብ በዓሉን ልዩ ለማድረግ እንቅስቃሴ ተጀምሯል፡፡ ካሁን በፊት የአዋሳ ምዕመናን ባዘጋጁት “አንድ አድርገን” በሚለው ቪሲዲ ላይ ዲ/ን ያሬድ አደመ የአውሮፕላኑ ግዢ ዋጋ ማቅረቢያ (proforma) እንደተሰበሰበ መናገሩ ይታወቃል፡፡ የበዓል አከባበር ኮሚቴው በዋናነት በወ/ሮ እጅጋየሁ በየነ የሚመራ ቢሆንም የኮሚቴው አፍአዊ ሰብሳቢዎች ሊቃነ ጳጳሳት እንዲሆኑ በመታሰቡ በጊዜአዊነት ሰብሳቢው ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡ በሊቀ ካህናት ጌታቸው ዶኒ እና በወ/ሮ እጅጋየሁ በየነ ዋና አስተባባሪነት በ18ኛው በዓለ ሲመት ፓትርያሪኩን “ሰርፕራይዝ” ለማድረግ ሐውልት እንዳሰሩላቸው በዓለ ሲመቱን በልዩ ሁኔታ እንዲከበር ጥረት እንዳደረጉ ወ/ሮ እጅጋየሁ ካሁን በፊት ከቁም ነገር መጽሔት ጋር ባደረገችው ቃለ ምልልስ ገልጻዋለች፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ ግን ሐውልት ማቆም እንኳንስ በቁም እያሉፉም ከቀኖና ቤተክርስቲያን ውጪ በመሆኑ እንዲፈርስ ወስኗል፡፡ ወ/ሮ እጅጋየሁ የ20 ኛውን ዓመት በዓለ ሲመት በድሚ የበለጠ ልዩ እና ታሪካዊ ለማድረግ ብርቱ ጥረት እያደረገች እንደ ሆነ የቤተክህነቱ ምንጮች የገለጹ ሲሆን የአውሮፕላኑ ግዢ ከተሳካና ከተፈጸመ ፓትርያርኩ የግል አውሮፕላን ያላቸው ብቸኛው አፍሪካዊ የሃይማኖት መሪ ይሆናሉ፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ በመጪው ጥቅምት ወር 2004ዓ.ም ለሚካሄደው የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ በርካታ ኤጲስ ቆጶሳትን ለመሾም ልዩ ኮሚቴ ተቋቁሟል፡፡ በቤተ ክህነቱ ሰዎች “ተለዋጩ ቋሚ ሲኖዶስ” የሚል ስያሜ ያገኘው እና ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ፣ ብፁዕ አቡነ ገሪማ፣ መጋቤ ምሥጢር ወልደ ሩፋኤል ፈታሒ፣ ንቡረ ዕድ ኤሊያስ አብርሓ እና የኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ሓላፊ እስክንድር ገብረ ክርስቶስ የሚገኙበት ኮሚቴ ተቋቁሟል፡፡ ይህ ኮሚቴ ነሐሴ 15 ቀን 2003 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ በመጪው ጥቅምት ወር በሚደረገው ሲኖዶስ ስብሰባ ኤጲስ ቆጶሳት ሹመት እንዲካሄድ እና ከአንድ ዓመት በኋላ ሊቃነ ጳጳሳት ለማድረግም ታቅዷል፡፡

Posted in ዜና | 69 Comments

ሃይማኖትና ፖለቲካ በኢትዮጵያ፡ የትውልድ ክፍተትና ግጭት ከኢ/ኦ/ተ/ቤ አንፃር

በአብዩ በለው ጌታሁን      (abiyuye@gmail.com) ኦገስት 2011, ኮሎምበስ, ኦሃዮ      ቀጣዩ ምዕራፍ እና    የመጨረሻው የኢት/ኦ/ተ/ቤ/ክ ወጣቱ ምዕመንና ሀገራዊ፣ ህዝባዊና፣ ሃይማኖታዊ ተሳትፎዎቹ 1. ነባራዊው ሃገራዊና ፖለቲካዊ ሁናቴ፡ የእኔ ትውልድ ታሪካዊ ተሳትፎና ድርሻ ታሪካችን እንደሚዘክረው የዘመኑ ወጣት፤ የ“እኔ ትውልድ” ቢያንስ የሁለት … Continue reading

More Galleries | Comments Off

በስም ማጥፋት ወንጀል ተጠርጥረው የተከሰሱት ሦስቱ መምህራን ፍርድ ቤት ቀረቡ

በሜቲ ኤጀታ (memettiej1@gmail.com) በጋሻው ደሳለኝ ስሜን በማጥፋት ከሰው ልቡና እንድወጣ አድርገውኛል በማለት አቤቱታ ያቀረበባቸው እነ መምህር ዘመንድኩን በቀለ ፍርድ ቤት ቀረቡ የአቡነ ጳውሎስ ደብዳቤ ማስረጃ ሆኖ ቀርቧል እነ በጋሻው የተሐድሶ መናፍቅነት አቀንቃኝ በሆነው‹‹ አሸናፊ ቦሻ ›› ላይ ተስፋቸውን ጥለዋል ዲ.ን … Continue reading

More Galleries | 7 Comments

አስቄጥሳዊ ራዕይ … ፍሬ ጎርጎርዮስ… ዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳም

This gallery contains 13 photos.

በማቴዎስ አጥምዛ (gebrher33@gmail.com) በረከታቸው ይድረሰንና ብጹዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ በአርቆ አሳቢነታቸው እና ወጣቱን ትውልድ ለቤተክርስቲያን ዓላማ በአንድ በማሰለፋቸው ዘወትር ሲታወሱ የሚኖር አባት ናቸው፡፡ለትውልዱ ትተው ካለፏቸው ትሩፋቶች መካከል ማኅበረ ቅዱሳን እና የዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ተጠቃሾች ናቸው፡፡ መሰንበቻውን ወደ … Continue reading

More Galleries | 7 Comments

ከአራት ሀገረ ስብከቶች ለተውጣጡ ‹‹የቤተክርስትያን አገልጋዮች›› የተሐድሶ ሠራዊትነት ስልጠና ተሰጠ

This gallery contains 3 photos.

በማቴዎስ አጥምዛ (gebrher33@gmail.com) የሥልጠናው ዋና ርዕሰ ጉዳይ ኢየሱስን ማለመመድ የሚል ነበር:: “ለሥልጠናው ተሳታፊዎችኢየሱስ አማላጅ ነው፡፡” የሚል ማስታወሻ እና መጸሐፍ ተሰጥቷቸዋል:: ከሠልጣኞቹ መካከል ቀደም ሲል ማኅበረ ቅዱሳን በክረምት ተተኪ መምህራን ሥልጠና አሰልጠኗቸው ከነበሩት ሠልጣኞች አንድ ግለሰብ ተገኝቷል:: በምስራቅ ኢትዮጵያ በሚገኙ አራት … Continue reading

More Galleries | 31 Comments

“መልአከ ገነት አባ” ናትናኤል መልአኩ ወደ ሱዳን ፈረጠጡ

This gallery contains 3 photos.

በሸዊት ገ/ኪዳን (shewitgbrkdn95@gmail.com) ጸሎት በእንተ ማኅበረ ቅዱሳን የሚል አነስተኛ ጽሑፍ በትነዋል፡፡ ወደ ሱዳን ለመውጣታቸው የቅዱስ ፓትርያርኩና የአቡነ ፋኑኤል እርዳታ እንዳለበት እየተወራ ነው:: ሀዋሳ ላይ ይኽንን ጽሐፍ የሚያሰራጩት በሕግ አካላት እየታደኑ ነው፡፡ ጥቂት የማይባሉ ወዳጆቻቸው በመፈረጠጣቸውና በበተኑት ተራ ጽሑፍ እጅ ግ … Continue reading

More Galleries | 26 Comments

የሐረሩ ስልጠናና የገብርኄር ሐሩር ውጤት

This gallery contains 7 photos.

በማቴዎስ አጥምዛ (gebrher33@gmail.com) ገበየሁ ይስማው ሥልጠናው መካሄዱን አመነ የሠልጣኖች ምልመላ ሂደትን አብራርቷል የምስራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ለጉባኤ ከአዲስ አበባ ሳባኪ እንዳይጠራ ወሰነ ማኅበረ ቅዱሳን በተሐድሶ ሰራዊትነት የሰለጠነ አባል የለኝም አለ ከድሬዳዋ ለተሐድሶ ሰራዊትነት ሥልጠና ወደ ሐረር የተጓዙ በሀሳብ ባለመግባባት ለሦስት … Continue reading

More Galleries | 20 Comments

ርዕሰ አንቀጽ- የሚያውኩአችሁ ይቆረጡ ገላትያ ፭÷፲፪

      የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ጥንታውያን ከሚባሉት እና የሐዋርያትን ትምህርት ከምንጩ ከተቀበሉት አብያተ ክርስቲያናት መካከል አንዷ ነች፡፡ ክርስትና ከስብከተ ወንጌል እና ከምእመናን ጉዞ ታሪክ በተለየ መልኩ የተጓዘውም በኢትዮጵያ ብቻ ነው፡፡ ክርስትና ለልማዱ የድሆች ሃይማኖት ነበር፡፡ ይህም ቀድመው ትምህርቱን የተቀበሉት ከምድረ ፍልስጤም ጀምሮ … Continue reading

More Galleries | 1 Comment

ሰበር ዜና ፡- ዲ/ን ዳንኤል ክብረት እና ማኅበረ ቅዱሳን የ2003ዓ.ም ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ተብለው ተመረጡ

This gallery contains 2 photos.

በሜቲ ኤጀታ (memettiej1@gmail.com) ዲ/ን ዳንኤል ክብረት ከአምስት ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች አንዱ ሲሆን ማኅበረ ቅዱሳን ደግሞ ከአምስት ተጽዕኖ ፈጣሪ ተቋማት አንዱ ሆኗል ዛሬ ጳግሜን 4 ቀን 2003 ዓ.ም ታትሞ የወጣው ፍትሕ ጋዜጣ ቅጽ 4 ቁጥር 152 በጋዜጣው አንባብያን እና ኤዲቶርያል ምርጫ … Continue reading

More Galleries | 36 Comments

ለተወደዳችሁ የገብር ኄር የጡመራ ሰሌዳ ወዳጆች

በእግዚአብሔር ፈቃድ የሙከራ ያልነው ጊዜ ተጠናቋል ስለ ነበረን ጊዜ ሁሉ እግዚአብሔር ይመስገን፡፡ ከዚህ ቀጥሎ የሙከራው ጊዜ እንዴት እንደነበረ እንገምግመው፡- ገብር ኄር የጡመራ ሰሌዳ በነሐሴ 3 ቀን 2003 ዓ.ም ለኢትዮጵያ እና ለኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ሁለንተናዊ እድገት በትጋት እንሰራለን በሚለው መሪ ቃል … Continue reading

More Galleries | 6 Comments

የብድር ዕድሜ

በርካታ ሰባክያን የተለያዩ ትምህርታዊ ጽሑፎችን ለጡመራ ሰሌዳችን በመላክ ላይ ይገኛሉ፡፡ የዲ/ን ምትኩ አበራ ጽሑፍ ወቅቱን የጠበቀ ሆኖ ስላገኘነው እንዲህ አቅርበነዋል፡፡ዲ/ን ምትኩ አበራ ለበርካታ ዓመታት በቤተከርስቲያን በተለያዩ የሓላፊነት ቦታዎች ተመድቦ ከማገልሉ በላይ በበሳል ስብከቶቹ የሚታወቅ መምህር ነው፡፡     በአብ ስም … Continue reading

More Galleries | 2 Comments

የማይታዩ እጆች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ላይ

This gallery contains 1 photo.

በሙላቱ ደቦጭ mulatudeboch@gmail.com አባ ሠረቀ ብርሃን ወልደሳሙኤል   (እምነት ሳይለይ የሚያገለግለው ካህን!)   የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጥንታዊት ታሪካዊትና አማናዊት ናት እየተባለ የሚነገረውን እውነት እየበለቱ ማሳየት ብቃቱ ባይኖረኝም እውነታው ግን ቅንጣት ታህል ሳልጠራጠረው የምቀበለው ነው፡፡        ዓለም አቀፋዊው ታሪክ እንደሚያስረዳን ይህቺ … Continue reading

More Galleries | 30 Comments

የአንዳንድ ሰው አልባ ብሎጎችና የነበጋሻውን ቅጥፈት ያጋለጠ የሐዋሳ ደብረ ምህረት ቅ/ገብርአል ቤተክርስቲያን ሰበካ ጉባኤ የአስመራጮች ምርጫ

ማቴዎስ አጥምዛ (gebrher33@gmail.com) ከሁለት አመታት የሀዋሳ ከተማ ብጥብጥ በኋላ ከተለያየ አካላት ታዛቢዎች በተገኙበት ማለትም ጠቅላይ ቤተ ክህነት ሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ ፪ ተወካዮችን – ከመንግስት ፪ – አንዲሁም ከሀገር ስብከቱ እና ወረዳ ቤተ ክህነት በተገኙት መስከረም 7 ቀን 2004 ዓ.ም … Continue reading

More Galleries | 8 Comments

የበጋሻው ደሳለኝ የብጥብጥ ሙሻአዙር ከደቡብ ወደ ምስራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት

This gallery contains 1 photo.

በማቴዎስ አጥምዛ (gebrher33@gmail.com) ጳጳሱ ፈሪ ናቸው አስፈራሯቸው….. በጋሻው ወንጌል እና ቅዳሴ አንድ ነው ………ብጹዕ አቡነ ያሬድ በብጹዕ አቡነ ዜና ማርቆስ ላይ ጫማዋን የወረወረች ቀንደኛ ሴትን ጨምሮ በርካታ የቀድሞ ተሐድሶዎች በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ላይ የተቃውሞ ድምጽ አሰምተዋል የምስራቅ ሐረርጌ እና … Continue reading

More Galleries | 30 Comments

ለሃይማኖት ሰባኪያን ፈቃድ ሊሰጥ ነው!!!!

በሜቲ ኤጄታ (memettiej1@gmail.com) በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን በኩል ፈቃድ የሚያገኙ ሰባኪያን በአብነት ትምህርት ቤት የተማሩ ወይም ከመንፈሳዊ ኮሌጆች በዲፕሎማ ወይም በዲግሪ የተመረቁ ብቻ ይሆናሉ፡፡ በተሰጠው ፈቃድ በአግባቡ የማያገለግል ሰባኪ ፈቃዱን እስከ መቀማት የሚደርስ እርምጃ ይወሰድበታል፡፡ ዛሬ መስከረም 12 ቀን 2004 ዓ.ም ታትሞ … Continue reading

More Galleries | 56 Comments

ወ/ሮ እጅጋየሁ በየነ “ሐውልቱ እስከ መቼ?” የሚል መጽሐፍ አሳተሙ

This gallery contains 1 photo.

ከእውነተኛዋ ደጀ ሰላም የተወሰደ መጽሐፉ የፕሮቴስታንታዊ-ተሐድሶ-ኑፋቄ አራማጅ ነው በሚባል ሰው የተዘጋጀ እንደሆነ ተነግሯል፤ * በመስቀል-ደመራ በዓል ዐውደ ትርኢት የሚያቀርቡ ወጣቶች የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ዋና ሓላፊን ጨምሮ ወ/ሮ እጅጋየሁ በየነ እና ሕገ ወጥ ሰባክያን በበዓሉ ላይ አንዳችም ተሳትፎ እንዳይኖራቸው አስጠንቅቀዋል፤ … Continue reading

More Galleries | 44 Comments

ሰበር ዜና ፡- ለረጅም ወራት ያለ ሰበካ ጉባኤ የቆየው የሀዋሳ ደ/ም/ቅዱስ ገብርኤል ገዳም አዲስ ሰበካ ጉባኤ ተመረጠለት፡፡

ማቴዎስ አጥምዛ (gebrher33@gmail.com) በምርጫው ሥነ ሥርዓት ከ1100 በላይ ምዕመናን ተገኝተዋል፡፡ እነ ያሬድ አደመ አመጽ ለማስነሳት ስላልቻሉ ከገዳሙ ሰ/ት/በት በሕገ ወጥ መንገድ የዘረፉትን ንዋያተ ማኅሌት ይዘው የግብር አጋሮቻቸው ወደ ሚገኙበት ማረሚያ ቤት አቅንተዋል፡፡  የሰጣችሁንን አደራ ያለ ማንም ተጽእኖ እና ጣልቃ ገብነት … Continue reading

More Galleries | 13 Comments

የመስቀል በዓል በመስቀል አደባባይ በታላቅ ድምቀት ተከበረ

ሸዊት ገብረኪዳን shewitgbrkdn95@gmail.com ፠ የተፈራው ረብሻአልነበረም ፠ አባ ሰረቀ በዓሉ ላይ ምንም ዓይነት ተሳትፎ አልነበረውም ፠ የአዲስ አበባ ሰ/ት/ቤት ወጣቶች ያስቀመጡት ቀድመ ሁኔታ ተተግብሯል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከሚከበሩት ዐበይት በአላት መካከል አንዱና ቁጥሩ በቱሪስቶቹ ዘንድ የአደባባይ በዓል(spiritual open air … Continue reading

More Galleries | 13 Comments

መስቀልና እመቤታችን

መስቀልና እመቤታችን በዲያቆን ኅብረት የሺጥላ (hibretyes@yahoo.com) ዲያቆን ኅብረት የሺጥላ በበሳል ኦርቶዶክሳዊ ስብከቱ በጠንካራ መንፈሳዊ ጽሑፎቹ የሚታወቅ መምህር ነው፡፡ እስካሁን ሕይወተ ወራዙት ፩ እና ፪ ፣ ትዳር እና ተላጽቆ፣  ውግዘት፣ ከማያምኑት ጋር እንዴት ? የተሰኙ መጻሕፍትን አበርክቷል፡፡ እነሆ በፌስ ቡክ ገጹ … Continue reading

More Galleries | 10 Comments

የድሬዳዋ ሀ/ስብከት በተሀድሶ መናፍቃን ዙሪያ ቁርጠኛ እርምጃ ለመውሰድ ሲወያይ ከምስራቅ ሀረርጌ ሀ/ስብከት ቀጥሎ ሁለተኛው ሆነ፡፡

This gallery contains 2 photos.

                                  በሸዊት ገብረ ኪዳን(shewitgbrkdn@gmail.com) •        “የድሬዳዋ ሀገረ ስብከት ራሱን ይፈትሽ” የድሬዳዋ  ሳባ ደ/ኃ/ ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ አስተዳዳሪ •       “መረጃውን ማነው የቀረፀው?” የድሬ ዳዋ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ •       በሐረር ከተማ ሁለተኛ ዙር … Continue reading

More Galleries | 4 Comments

ተሐድሶን በዜና¡

ሙሉቀን መንቻሞ (muluqenm99@gmail.com) ተሐድሶነት እና የተሐድሶ እንቅስቃሴ የሰሞኑ የቤተክርስቲያን አብይ ጉዳይ ሆኗል እንግዲህ እኔስ ምን ቀረኝ ሰው ሁሉ ስለሚወያይበት ጉዳይ ብጽፍ ምን አለበት? እኔን በተለይ ይህንን ጽሑፍ እንድጽፍ ያደረገኝ የወዳጆቼ እና “ገብር ኄር” የጡመራ ሰሌዳን በጋራ ለመጀመር ከተስማማነው የሜቲ እና … Continue reading

More Galleries | 9 Comments

ሰበር ዜና- ሐረር ሐዋሳን እየመሰለች ነው፡፡

ማቴዎስ አጥምዛ (gebrher33@gmail.com) ዲ/ን በጋሻው እና ግብር አበሮቹ በሐዋሳ ከተማ ያደረጉት እና በቁርጠኛ ምዕመናን እና የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች የከሸፈው የማበጣበጥ ስራ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ወደ ሐረር ከተማ ማዛወራቸው የሚታወቅ ሲሆን ዲ/ን በጋሻውም ግለሰቦቹን በማደራጀት እና መመሪያ በመስጠት ቀጥተኛ ተሳትፎ … Continue reading

More Galleries | 11 Comments

ከፊትዎ ይቁረሱ

የተወደዳችሁ አንባብያን ፍቅር በእምነት fikerbemnet@yahoo.com.au የተባሉ አንባቢያችን የላኩልንን ጽሑፍ እንደሚከተለው አቅርበነዋል፡፡ በተነሳው ጉዳይ ላይ ተመሳሳይ ወይም የተለየ ሐሳብ ላላችሁ የሰሌዳው አንባብያን ሐሳባችሁን መስጠት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡ እኛ ነፍሳቸውን ሊያድኑ ከሚያምኑት ነን እንጂ ወደ ጥፋት ከሚያፈገፍጉት አይደለንም ዕብ 10-39 አንዳንድ ካህናት … Continue reading

More Galleries | 27 Comments

በቤተክርስቲያናችን ጉዳይ ዝም ማለት አንችልም

የተወደዳችሁ አንባብያን ማኅበረ በዓለ ወልድ ከሰሜን አሜሪካ በወቅታዊ የቤተክርስቲያን ጉዳዮች ላይ ያወጣውን የአቋም መግለጫ በአድራሻችን የላከላን በመሆኑ እንደሚከተለው አቅርበነዋል፡፡ ማኅበሩ በሰሜን አሜሪካ እና በኢትዮጵያ ባሉ ገዳማት ላይ የልማት እና የበጎ አድራጎት ሥራዎችን በመሥራት የሚታወቅ ማኅበር ነው፡፡                                                                     መስከረም 29 ቀን2004ዓ.ም. … Continue reading

More Galleries | 15 Comments

በአባ ሠረቀ ብርሃን እና በማኅበረ ቅዱሳን መካከል የተፈጠረውን አለማግባባት እንዲያጣራ የተሰየመው ኮሚቴ እንቅስቃሴ አጭር ሪፖርታዥ!!

በሜቲ ኤጀታ (memettiej1@gmail.com) የማህበረ ቅዱሳን ደንብ መሻሻል አለበት ……. አቡነ ገሪማ ከኃላፊነቴ የምነሳ ከሆነ ከአገር ወጥቼ ቤተክርስቲያንን እገነጥላለሁ….. አባ ሠረቀ አባ ሠረቀ እየፈጠነ ብዙ ችግር ውስጥ ከቶኛል……. አባ ጳውሎስ የማኅበሩን መተዳደሪያ ደንብ የሚያሻሽል ኮሚቴ እንዲያቋቁም ለቅዱስ ሲኖዶስ የውሳኔ ሃሳብ እናቀርባለን….. … Continue reading

More Galleries | 11 Comments

የደሴ ክርስቲያኖች በተስፋ መቁረጥ ላይ ናቸው!!!

ደሳለኝ ገዜ gezegebrher@gmail.com ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት በምእመናን እና በአገልጋዮች ካህናት ላይ እየፈጸመ ያለው የአስተዳደር በደል ከልክ እያለፈ መጥቷል፡፡ ምእመናን እና ካህናትም ወደ መደበኛ ፍትሕ ሰጪ አካላት አቤት ቢሉም ውሃ የሚያነሳ መፍትሔ ሊያገኙ አልቻሉም፡፡ ለዚህ ማሳያ የሚሆን … Continue reading

More Galleries | 12 Comments

የቤተክርስቲያን አስተዳደር መሻሻል- ለዘርፈ ብዙ ችግሮች ዘላቂ መፍትሔ

This gallery contains 4 photos.

ቀሲስ እንጂነር ወንድምስሻ አየለ የላኩልንን ጽሑፍ ወቅታዊ እና አስፈላጊ በመሆኑ እንዲህ አውጥተነዋል፡፡ wendemseshaa@yahoo.com wendemsesha.kesis@facebook.com   የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ራስዋን የቻለች ዓለም አቀፍ ተቋም መሆኗ እንዲሁም ቀኖናዊነትን አጽንቶ የዛሬውን ትውልድ ለመምራት ጥብቅና ዘመናዊ አስተዳደር እንደሚያስፈልጋት ይታወቃል፡፡ ይህ አለመሆኑ በየአጋጣሚውና በሚገባውም … Continue reading

More Galleries | 11 Comments

ለ18ኛው የልጅ ልጄ ስለአባታችን አቡነ ጳውሎስ ሐውልት የተፃፈ ማስታወሻ

This gallery contains 2 photos.

ከኢ/ር ደጀኔ ቀልቤሳ  የተወሰደ አባታችን አቡነ ጳውሎስ መንበረ ፓትርያርኩን በተቆጣጠሩ 19ኛ ዓመት: ሐውልታቸው በቆመ በ1 ዓመት ከ3 ወሩ: ቅዱስ ሲኖዶስ ሐውልቱ በ20 ቀናት ውስጥ እንዲፈርስ በወሰነ በ1ኛው ዓመት በወርሃ መስከረም በወሩም በ29 ቀን ተፃፈ በ18ኛው የቅድመ ቅድመ አያትህ በደጀኔ:: 18ኛው … Continue reading

More Galleries | 11 Comments

የተሃድሶ ትንቅንቅ ሲኖዶስ ሲቀርብ በሰሜንና በምስራቅ

This gallery contains 1 photo.

  በፍቅር ሃለፎምfkrhalefom95@gmail.com . የጎንደር ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን የተሐድሶ መናፍቃንን ሴራ የሚያጋልጥና ወቅታዊ ሥልጠና   ተሰጣቸው . የሐረርን ተሃድሶ ቡድን  አቡነ ጳውሎስ አነጋገሩ . በጋሻ ከአባጳውሎስ ጋር የታረቅኹት በሁለታችንም መሀል ያለው ሰው እንዳይጎዳ ነው አለ . የድሬዳዋ ሀገረ ስብከት የተሃድሶ አጣሪ … Continue reading

More Galleries | 10 Comments

የሰሜን አሜሪካ ዲሲ አካባቢ ሀገረ ስብከት ሰራተኞች እና ምእመናን የፓትርያርኩን ህገ ወጥ አሰራር የሚቃዎም የአቋም መግለጫ አወጡ፡፡

፠የሰሜን አሜሪካ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም በጥቅምቱ ሲኖዶስ እንደማይገኙ ገለጹ፡፡ ፓትርያርኩን “……ለስራና ለልማትና ሊጠሩኝ ሲገባ እንዴት ለበቀል ይጠሩኛል፡፡….. “ ብለዋቸዋል፡፡

        ፠ አዋሳንና አካባቢውን ለተሀድሷውያን ለማስረከብ ሲሰሩ የነበሩትና በአዋሳ ምእመናን እልህ አስጨራሽ መንፈሳዊ ትግልና በቅዱስ ሲኖዶስ ጠንካራ ውሳኔ ከቦታው የተወገዱት አቡነ ፋኑኤል ዲሲና አካባቢውን የማተራመስ ተግባራቸውን በትጋት ቀጥለውበታል፡፡

       ፠ያለ ቅዱስ ሲኖዶስ ዕውቅና በፓትርያርኩ ቀላጤ ደብዳቤ ብቻ የተከፈተው የውጭ ጉዳይ ጽ/ቤት እና ተወካዩ የተሀድሶ አቀንቃኙ ሊቀ ስዩማን ኃይለ ጊዮርጊስ ሞገስ በመግለጫው ክፉኛ ተቃውሞ ገጥሟቸዋል፡፡

 ፠በሰሜን አሜሪካና አካባቢው የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ካህናት፣ የሰበካ ጉባዔ አባላትና ምዕመናን በዋሽንግተን ዲሲ መንበረ ጵጵስና ባደረጉት ጠቅላላ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባዔ ላይ ድርጊቱን በይፋ ተቃውመውታል፡፡ ውሳኔያቸውንም ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ልከዋል፡፡

ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን መረጃዎች በቤተክህነት ዘጋቢያችን በሸዊት ገብረ ኪዳን የደረሱን ሲሆን ዝርዝሩን እናቀርባለን:: ጠብቁን፡፡  

Posted in ሐተታ | 1 Comment

የዋሽንግተን ዲሲ ጉባዔ ውሳኔ ለጥቅምቱ ሲኖዶስ አጀንዳ ይሆን ይሆን?

This gallery contains 2 photos.

  በሸዊት ገብረ ኪዳን shewitgbrkdn95@gmail.com      መስከረም 26እና 27 2004 ዓ.ም. የዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ሀገረ ስብከት አጠቃላይ የሰበካ መንፈሲዊ ጉባዔ እንደ አዲስ አበባው ያለፉት ጉባዔያት በጭቅጭቅ ተጀምሮ በጭቅጭቅ አልነበረም የተቋጨው ይልቁንም ለፊታችን ጥቅምት ሲኖዶስ የቤት ሥራ የሚሆን ውሳኔዎችን አሳልፎ እንጂ፡፡  … Continue reading

More Galleries | 9 Comments

በእንተ ስማ ለማርያም

This gallery contains 1 photo.

      ኢ/ር ደጀኔ ቀልቤሳ የላኩልንን መልእክት እንዲህ አቅርበነዋል:: ኢ/ር ደጀኔ ቀልቤሳ በቤልጀም ሀገር የማስተርስ ዲግሪ ሁለተኛ ዓመት ተማሪ መሆናቸውን ለመረዳት ችለናል:: ደጀኔን እናመሰግናለን፤ ወደፊትም እንደማይለዩን ተሰፋ እናደርጋለን፡፡        አንድ ቀን ከአንዱ ባልንጀራዬ ጋር ቁጭ ብለን ሻይ ቡና እያልን  በመሃል “አንተ … Continue reading

More Galleries | 15 Comments

እንዲህም ሆነ

በማቲዎስ አጥምዛ አንድ ግለሰብ ወደ ምዕራብ ሐረርጌዋ ሂርና ከተማ መጣ ሥልጣነ ክህነትም አለኝ በማለት በከተማ ውስጥ ወደሚገኘው ጥንታዊው ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን በመግባት ማገልገል ጀመረ እስካሁን ድረስ ከየት መጣህ? ሥልጣነ ክህነት የሰጠህ ሊቀ ጳጳስ ማን ነው? ከየትኛው የአብነት ትምህርት ቤት ተማርክ? … Continue reading

More Galleries | 3 Comments

እነ በጋሻው ከመንግስት መስሪያ ቤት የፍቃድ ደብዳቤ ገዙ

This gallery contains 5 photos.

 በሸዊት ገብረ ኪዳን(shewitgbrkdn95@gmail.com)                       እነበጋሻው ደሳለኝ ህገወጥ ሰባኪ ተብለው ከማህበረሰቡ እየደረሰባቸው ያለውን ተቃዎሞ ስላልቻሉት እንዲሁም የምስራቅ ሀረርጌ ሀገረ ስብከት ህገወጥ ሰባኪያንን አስመልከቶ ያስተላለፈውን መመሪያ ማለፍ ስላቃታቸው የባቢሌ ወረዳ ቤተ ከህነትን ወደጎን በመተው ማህበረ እስጢፋኖስ ቁጠር 2 … Continue reading

More Galleries | 5 Comments

በኢትዮጵያና በመላው ዓለም የምንገኝ የዓለም የተዋሕዶ ቤተሰብ

ጥቅምት 3ቀን2004 ዓ.ም. ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ አዲስ አባባ፣ ኢትዮጵያ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን “ለቅዱሳን አንድጊዜ ፈጽሞ ስለ ተሰጠች ሃይማኖት እንድትጋደሉ እመክራለሁ” ይሁዳ ፩ ፥ ፳ ይድረስ ለቅዱስ ሲኖዶስ የከበረ ሰላምታችንን በእግዚአብሔር ስም … Continue reading

More Galleries | 6 Comments

የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ 30ኛ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ዛሬ ተጀመረ

This gallery contains 1 photo.

       ሸዊት ገብረኪዳን shewitgbrkdn95@gmail.com በአዲስ አበባ የመንበረ ፓትርያርክ የስብሰባ አዳራሽ የሚካሄደው ይህ ጉባኤ ከተያዘለት መርሐግብር ዘግይቶ ቢጀመርም ቅዱስነታቸውን ጨምሮ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትና  ጳጳሳት የተገኙ ሲሆን በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ገዳም ካህናት በጸሎተ ወንጌል ተከፍቷል፡፡ ከሁሉም በፊት በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ሥራ … Continue reading

More Galleries | 2 Comments

ቀጥሎ የዋለው ጉባዔና የበሩ ላይ ጭቅጭቅ

This gallery contains 1 photo.

  በሸዊት ገብረ ኪዳን(shewitgbrkdn95@gmail.com)              ፴ኛው የመንበረ ፓትርያርክ ሰበካ መንፈሳዊ መደበኛ ስብሰባ ዛሬ ከሰዓት በኋላም ቀጥሎ ውሏል፡፡ ለጉባዔው ተሳታፊዎች በታደለው መርሐ ግብር መሰረት፤ የትግራይ ማዕከላዊ ዞን(አክሱም)፣የሲዳሞ፣የሰሜን ጎንደር፣የምስራቅ ሐረርጌ፣የጅማ ዞን፣የመቀሌ ዞን፣የኢሉባቡር፣የድሬዳዋ፣የጋሞጎፋ፣የሰሜን ወሎ፣የባሌ፣የደቡብ ጎንደርና የምሥራቅ ወለጋ አህጉረ ስብከቶች የ2003ዓ.ም.የስራ ሪፖርቶች በየተራና … Continue reading

More Galleries | 2 Comments

መጥፎ ሰው አልይ ብለህ አይንህን አትጨፍን

ዲ/ን ኢ/ር መላኩ ተስፋዬ ባለፈው የተለያዩ ወንድሞች ከላኩልን ለያት ያለ መልእክት የላኩልን ሲሆን ኢ/ር መላኩን እያመሰገን እንዲህ አቅርበነዋል አንባቢያን አስተያየት እንዲጡበት እንጋብዛለን፡፡ መላኩ ተስፋዬ (mlakutsfy@gmail.com) የቤተክርስቲያንን አስተዳደር አስመልክቶ ብዙ ብዙ እየተባለ ነው፡፡ አሁንም ለዚህ ጽኹፍ መነሻ የሆነኝ ወዳጄ ደጀኔ በእንተ … Continue reading

More Galleries | 5 Comments

የመንበረ ፓትርያርኩ ስብሰባ እንደቀጠለ ነው

በሸዊት ገብረ ኪዳን(shewitgbrkdn@gmail.com) · የቤተ ክርስቲያኗ ቃለ ዓዋዲ በኢትዮጵያ ሕግ ተቀባይነት ያገኝ  ዘንድ ተጠየቀ                                                                       . በባሕር ዳር የመናፍቃን ሠርግ ላይ ተገኝተው ሲጨፍሩ ለታዩት የተሐድሶ መናፍቃን የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ የማይረባ  ማስተባበያ ሰጡ፤ ·  ሁለት የመናፍቃን አዳራሽ ተዘግቶ በቦታው ላሉ … Continue reading

More Galleries | 3 Comments

ሰበር ዜና፡- የማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ ዛቻ እና ማስፈራሪያ ደረሰባቸው!!

በሜቲ ኤጄታ (memettiej1@gmail.com) ጥቅምት በባተ በሰባተኛው ቀን ከቀኑም በዘጠኝ ሰዓት የአሲራ መቲራ ‹‹አበ ምኔት›› ለማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ ለሊቀ ትጉኃን ቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ ስዩም ወንድ መሆናቸውን ማኅበሩ ጽሕፈት ቤት ድረስ በማምራት አስረዱ፡፡ መቼም የማይሰማ ጉድ እና የማይታይ ተአማር ሳይከሰት ውሎ ማደር … Continue reading

More Galleries | 19 Comments

ሰበር ዜና፡-እነበጋሻው ሰላማዊ ሰልፍ ሊያደርጉ ነው

በማቴዎስ አጥምዛ (gebrher33@gmail.com) በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ደቀመዛሙርት ከሆኑት ወዳጆቼ  ያገኘሁት መረጃ ቀንደኞቹ የተሐድሶ አቀንቃኞች በጋሻው አሰግድ እና ግብርአበሮቹ የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ መጀመሩን አስመልክቶ በሚደረገው የብጹአን አባቶች የጸሎት ስነስርዐት ላይ ሰላማዊ ሰልፍ ሊወጡ ነው፡፡ የኮሌጁ መደበኛ ተማሪዎች የደንብ ልብስ የሆነውን … Continue reading

More Galleries | 20 Comments

ይድረስ ለዲያቆን መላኩ

   በዲ/ን ኢ/ር በላኩ ተስፋዬ መልእክት ላይ የተላክ አስተያየት ደርሶናል የላኩትን እናመሰግናለን ኢ/ር መላኩም ይመለከቱታል ብለን ተስፋ እናደረጋለን፡፡   mistere    ( bmistere@yahoo.com)                                     … Continue reading

More Galleries | 3 Comments

የተሐድሶዎች ዘመቻ ፊልጶስ በአራት ኪሎ ነገ ሊታይ ነው

በሙላቱ ደቦጭ (mulatudeboch@gmail.com) ተሹሜ ወደ አሜሪካን እመለሳለሁ በማለት አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡ ፓትርያሪኩ ፈቅደውልኛል በማለት የግል አብያተክርስቲያናት እየከፈቱ ነው እነበጋሻው ቅዳሜ ለሚያደርጉት ሰልፍ ከአዋሳ, ክብረመንግስት እና ከሐረር ደጋፊ ጠርተዋል የአዲስ አበባ ሰ/ት/ቤት አባላት እና ኦርቶዶክሳዊ ሰባክያን ነገ ቅዳሜ ሰልፍ ያደርጋሉ ብፁዕ … Continue reading

More Galleries | 8 Comments

፴ኛውን የሰባካ መንፈሳዊ ጉባኤ ማጠቃለያ እና የኔ ትዝብት

           በሸዊት ገብረ ኪዳን(shewitgbrkdn95@gmail.com)        ፴ኛውን አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ አስመልክቶ ከመክፈቻው ሰዓት ጀምሮ ስጽፍ መቆየቴ ይታወቃል፡፡አሁን ስብሰባው በመጠናቀቁ ማክተሚያውን እነሆ፡፡            በቤተ ክህነቱ ወዳጄ ምክንያት የግብዣ ካርድ በማግኘቴ እንኳንስ ስብሰባውን ያን ውሻ ከቁልቁለት የማትጎትተውን የሥጋና የእንቁላል ሳንዲዊች ሳያመልጠኝ ሙሉውን … Continue reading

More Galleries | 10 Comments

ወንጀለኛው ማን ነበረ???

This gallery contains 1 photo.

በምሐባው ዓለሙ ሐምሌ 2003 ዓ.ም 180 ገጽ በቤተክርስቲያን ብልሹ አሰራርና ሙስና  ላይ ያነጣጠረ መጸሐፍ መጻፋቸው ይታወሳል በመሆኑም  ይህንን ተከትሎ የደረሰባቸውን ወንጀለኛው ማነው ብለው ጽፈውታል አንባቢያን ችገሩን (የደረሰባቸውን) እንዲትመልከቱት መጸሐፍንም ገዝታችሁ እንድታነቡ እጋብዛለን ፡፡       መስከረም 16 ቀን 2004 ዓ.ም. የመስቀል … Continue reading

More Galleries | 8 Comments

መቶ ሺኛው አንባቢ

የተወደዳችሁ የገብር ኄር የጡመራ ሰሌዳ አንባብያን! የሙከራ ያልነው ጊዜ ተጠናቆ በይፋ ተጀመረ ካልንበት ከመስከረም 1 ቀን 2004ዓ.ም አንስቶ የተለያዩ መረጃዎችን ወደናንተ ማድረሳችን ይታወቃል፡፡ ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ የመጣው የአንባብያን ቁጥር እነሆ 100000 (አንድ መቶ ሺ ) ደርሷል፡፡ ምናልባት ይህ ጽሑፍ በሚጻፍበት … Continue reading

More Galleries | 11 Comments

አቡነ ጳውሎስ የሀዋሳው ተሐድሶ ክንፍ የላካቸውን ልኡካን አነጋገሩ!!

Shewitgbrkdn95@gmail.com ፓትርያርኩ የቋሚ ሲኖዶስ አባላትን ያለ መሰብሰቢያ የጊዜ ሠሌዳ ስብሰባ ጠርተዋል አቡነ ገብርኤል አቡነ ጋዳፊ ተብለው ተጠርተዋል … በአቡነ ፋኑኤል ላይ ስልታዊ መፈንቅለ መንበረ  ጵጵስና ወይም ኩዴታ አደርገዋልም ተብለዋል፣ ብፁዕ አቡነ ፊሊጶስ፣ ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ፣ ብፁዕ አቡነ ሉቃስ እና ዶ/ር … Continue reading

More Galleries | 41 Comments

‹‹አባ›› ገ/መድኅን ….. ዐቃቤ ሕግ ገመቺስ …. እና የማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ….!!!!

በሜቲ ኤጄታ (memettiej1@gmail.com) • የማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ በተፈጸመባቸው ወንጅል መብታቸውን በሕግ እንዳያስከብሩ ጉዳዩን    በያዘው ዐቃቤ ሕግ ከፍተኛ ጫና እየደረሰባቸው ነው፡፡ • ‹‹አባ›› ገ/መድኅን ገ/ጊዮርጊስ ያቀረቡት አቤቱታ ውድቅ ሆነባቸው፡፡ •ማኅበረ ቅዱሳን ተከሶ እንጂ ከሶ በፍርድ ቤት ተወስኖለት አያውቅም፡፡ ስሜ ጥፍቷል ያሉት … Continue reading

More Galleries | 17 Comments

የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ፡ 19 ለ 1

ሸዊት ገብረኪዳን (shewitgbrkdn95@gmail.com) • አጣሪ ኮሚቴው የአባ ጳውሎስን ፕሮግራም ብቻ ነው ያቀረበው • አቡነ ሕዝቅየል የቡድን ስራ ሆኖብኝ እንጂ ‘ሰውየው’ ጴንጤ ነው • አባ ጳውሎስ ለብዙዎች አባቶች ስልካችሁ ተጠልፏል በማለት እያስፈራሩ ነው • ማህበረ ቅዱሳን ከቀረጥ ነጻ ያስገባል ከተባለ መንግስት … Continue reading

More Galleries | 13 Comments

ሰበር ዜና ቅዱስ ሲኖዶስ አባ ሰረቀ ብርሃንን አባረረ

በሸዊት ገብረ ኪዳን(shewigbrkdn95@gmail.com)

አባ ሰረቀ ብርሃን ወ/ሳሙኤል

አባ ሰረቀ ብርሃን ወ/ሳሙኤል

ማህበረ ቅዱሳንን ስም በማትጥፋቱ የአዲስ አበባ 131 ሰ/ት/ቤቶች በምንፍቅናው የከሰሱት  አባ ሰረቀ ብርሃን ወደል ሳሙኤል ዛሬ ቅዳሜ ከሥልጣናቸው እንዲወርዱ ቅ/ሲኖዶስ ወሰነባቸው። ከሥልጣናቸው መነሣትችም ብቻ ሳይሆን ለረዥም ጊዜ በሚከሰሱበት ከኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ እምነት ውጪ ነው  የሚባለውን እምነታቸውን የሚመረምር አምስት ሊቃነ ጳጳሳት የሚገኙበት ኮሚቴም ተሰይሟል። የኮሚቴው አባላትም ብፁዕ አቡነ  ናትናኤል፣ ብፁዕ አቡነሕዝቅኤል፣ ብፁዕ አቡነ እንድርያስ ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ፣  እና ብፁዕ አቡነ ያሬድ ናቸው ፡፡ እኛም ከዚህ በኋላ በእሳቸው ላይ ያለንን መረጃ እንጽፋለን የዚህን ዜና ዝርዝርም እናቀርባለን፡፡

እግዚአብሔር ቤተክርስቲያናችይጠብቅልን!!!

Posted in ሐተታ | 20 Comments

ቅዱስ ሲኖዶስ አዲሱን የውጭ ጉዳይ ተጠሪ ቢሮ እንዳይሞት እንዳይድን አደረገው::

በሸዊ ገብረ ኪዳን(shewitgbrkdn95@gmail.com)      

         ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ በሰሜን አሜሪካ የዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም እና የካሊፎርኒያ እና አካባቢው አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አዎስጣቴዎስን ለመጉዳት በማሰብ ያቋቋሙት የውጭ ጉዳይ ተጠሪ ቢሮ ተጠንቶ ለሶስቱም ሊቃነ ጳጳሳት ተጠሪ እንዲሆን ያለበለዚያም እንዲዘጋ ተወሰነ፡፡ ቅዱስ ፓትርያርኩ ይህንን ውሳኔ ለማስቀልበስ  እያደገ የመጣውን የስብከተ ወንጌል አገልግሎት ለማጠናከር እና አሁን ያለው አደርጃጀት ለመንግስት አለመመቸቱን እንዲሁም ሌሎች ማደናገሪያ ምክንያቶችን ቢያቀርቡም ቅዱስ ሲኖዶስ ሳይቀበላቸው ቀርቷል:: አቡነ ፋኑኤል እሾምበታለሁ ብለውበት የነበረው በሰሜን አሜሪካ የዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው እንዲሁም የካሊፎርኒያ እና አካባቢው አህጉረ ስብከት ሊቃነ ጳጳሳት መነሳታቸው ቀርቶ ሁለቱም ሊቃነ ጳጳሳት ቀርበው ለቀጣዩ የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ሃሳባቸውን እንዲያስረዱ በመወሰን ቅዱስ ሲኖዶስ አጀንዳውን ዘግቶታል ፡፡

በተያያዘ ዜና ቅዱስ ፓትርያርኩ ከእማትርያሪኳ ወ/ሮ እጅጋየሁ ጋር በመመካከር በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አሳቦ አቡነ ሳሙኤልን ለመምታት ያዘጋጁት ሪፖርት ከቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ጠንካራ ተቃውሞ በማስነሳቱ ሳይሰማ ቀርቷል:: በተለይም ደግሞ አቡነ ሳሙኤል “ኦዲት መደረግ ካለበት ከፋንታሁን ሙጬ ጀምሮ ለእርሰዎ ያላግባብ እስከተገዛው መኪና ድረስ ነው” በማለት ተቃውመውታል:: ሌሎችም ብጹአን አባቶች “መደረግ ካለበት ማዘዝ ያለበት ቅዱስ ሲኖዶስ እንጂ እርሰዎ አይደሉም” በማለት ውድቅ አድርገውታል፡፡  በአጠቃላይ በዚህ ጉባኤ የተሻሉ ውሳኔዎች የተወሰኑበት አባቶችም ከመቼውም ጊዜ በላይ የጠነከሩበት ነበር ማለት ይቻላል፡፡ የአቡነ ማርቆስ አድር ባይነት ይሁን አንዳች የጥቅም ትስስር በሁሉም አጀንዳዎች ላይ በነበሩ የሀሳብ ልውውጦች በአቡነ ጳውሎስ ላይ መለጠፍ ብጹአን አባቶችን አሳዝኗል::

እግዚአብሔር ቤተክርስቲያናችንን ይጠብቅልን

Posted in ዜና | 5 Comments

የቅዱስ ሲኖዶስ የዛሬ ውሎ ለተሃደረሶዎች ሀዘንና ደስታ

በሸዊት ገብረ ኪዳን (shewitgbrkdn95@gmail.com)
አቡነ ፈኑኤል እንዳሉት የአሜሪካ ሁለቱ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሆኑ
እነበጋሻው ደሳለኝ እና ሌሎች ሰምንት ሰዎች ተሃድሶ ተሃድሶ ነው በማለት የአባ ሰረቀን እንዳዩ የተሰየሙት እንዳዩት ቅዱስ ሲኖዶስ ወሰነ
ሰሜን አመሪካ እረብሻ ተነስቷል አቡነ ፋኑኤል የራሱ ካላቋቋመ እሚቀበለው የለም ተብሏል
“እስካሁን የሚበድሉን አቡነ ጳውሎስ ነበሩ አሁን ግን ሲኖዶስ በደለን” የአሜሪካ ምእመናን
“ቅዱስ ሲኖዶስ አቡነ “ሳጥናኤልን”ና አቡነ ሕዝቅየልን ከሚያረግብን ለምን ዝምብሎ አያወግዘንም” እነበጋሻው

ዛሬ ቅዱስ ሲኖዶስ አቡነ ፋኑኤል እንደተናገሩት ሰሜን አሜሪካን ሁለት ሀገረ ስብከት በዶላር የገዙ ሲሆን በቀጣይ ብፁዕ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ ከባሌ ጋራ ደርበው ወደያዙት ጉጂ ቦረና/ሊበን/ ሀ/ስበከት እንደሚዛወሩ፣ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የባሌ ሀ/ስብከትን እንደሚይዙ፤ ብፁዕ አቡነ አብርሃም ደግሞ ምሥራቅ ሐረርጌ እና ጅጅጋ አህጉረ ስብከት እንደሚሾሙ ተነግሯል፤ ምሥራቅ ሐረርጌ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ያሬድም ወደ ሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳይ ኮሌጅ ሊቀ ጳጳስ ሆነው ይዛወራሉ፤ ያረፉት ብፁዕ አቡነ በርናባስ በነበሩበት ምዕራብ ጎጃም ሀ/ስብከት የምሥራቅ ጎጃም ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ተመድበዋል፤ በእርሳቸው ምትክ የአዊ እና መተከል አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማርቆስ የተመኙትን ባይሆንም ምሥራቅ ጎጃምን ደርበው ይመራሉ፡፡ አቡነ ዳንኤል አሰበ ተፈሪ ደርሶቸዋል ግን እስካሁን አልቀበልም እያሉ ነው ምስራቅ አፍሪካን የደቡብ አፍሪካው ስማቸያላስታወስናቸው ይዘውታል፡፡ ባጠቃላይ እነ በጋሻው ደሳለኝ የነሱን ጉዳይ እንዳዩ  እነ አቡነ ናትናኤል ፣ቄሪሎስ፣ ሕዝቅየል፣ እንዲርያስ፣ ያሬድ በመሾማቸው ያዘኑ እንደውም እያለቀሱ ቢሆንም አቡነ ፋኑኤል አሜሪካ በመሾማቸው ተደስተዋል ካሁኑ አብረን ነው እያሉ ስለሆ ባሁኑ ስዓት እጅጋየሁ እናያሬድ አደመ አቡነ ፋኑኤል ቤት እየዶለቱ ይገኛሉ አንዳንድ አባቶች ሰሜን አሜሪካ ላይ ስህተት ሰራችሁ ሲበሉ የተናገሩት ደግሞ ለፋኑኤል እንከራከር ህዝቡ ለሚያበረው ብለዋል!!

 ዝርዝሩን እናቀርባለን

Posted in ሐተታ | 11 Comments

ማን ከማን ጋር ነው?

This gallery contains 1 photo.

በፍቅር ሀለፎም fkrhalefom95@gmail.com (አነጋጋሪውን ቪሲዲ ማን ለቀቀው?) እርግጥ ነው፤ እገሌ የተሐድሶን አጀንዳ እያስፈጸመ ነው፡፡እሺ እገሌስ?እነ እገሌስ ለይቶላቸዋል፤ እነ እገሌስ?….ይኽ ማን ከማን ወገን እንደሆነ ለማወቅ የሚቀርብ የየአካባቢው ጥያቄ ነው፡፡ ይኽ ጥያቄ ተመልሷል፡፡ መላሹ ክፍል ደግሞ ራሳቸው ተጠርጣሪዎቹ ናቸው፡፡ሌላውን ሰው በጥርጣሬ ዓይን … Continue reading

More Galleries | 29 Comments

የዛሬ ጥቅምት 25 ቀን2004 የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ

በሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ እና በማኅበረ ቅዱሳን መካከል የተፈጠረው የሥራ አለመግባባት እና ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን በተመለከተ አለ የተባለው ችግር ከቅዱስ ሲኖዶስ አባላት የተመረጡ ሊቃነ ጳጳሳት ተጣርቶ ይቀርብ ዘንድ መመሪያ ተሰጥቷል በ1991 ዓ.ም የተሻሻለውና እየተሠራበት የሚገኘው ቃለ ዐዋዲ ለሦስተኛ ጊዜ ተሻሽሎ … Continue reading

More Galleries | 13 Comments

ሰበር ዜና ፡- ብጹዕ አቡነ ፊሊጶስ መልቀቂያ አስገቡ!!!

በሸዊት ገ/ኪዳን (shewitgbrkdn95@gmail.com) የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብጹዕ አቡነ ሕዝቅኤል መልቀቂያ ለማስገባት በዝግጅት ላይ ናቸው ፡፡ አባ ሠረቀብርሃን የጠቅላይ ቤተ ክህነት ምክትል ሥራ አስኪያጅ እንዲሆን ከአቡነ ጳውሎስ ደብዳቤ ደርሶታል፡፡ ፓትርያርክ ጳውሎስ ብጹዕ አቡነ ፊሊጶስን በማግባባት ላይ ናቸው፡፡ አቡነ ጳውሎስ አባ … Continue reading

More Galleries | 12 Comments

‹‹አባ›› ሠረቀ በሕገ ወጥ መንገድ ከተሾመበት ኃላፊነት ተነሳ!!!

በሸዊት ገ/ኪዳን(shewitgbrkdn95@gmail.com) ‹‹አባ›› ሠረቀ በሕገ ወጥ ማንገድ ከተሾመበት የጠቅላይ ቤተ ክህነት ምክትል ሥራ አስኪያጅነት ተነስቶ የሰበካ መንፈሳዊ ጎባዔ ማደራጅ መምሪያ ኃላፊ ሆነ ፈንታሁን ሙጬ የጠቅላይ ቤተክህነት ምክትል ሥራ አስኪያጅ ሆነ ሕገ ቤተክርስቲያን ከሚሻር ስልጣኔ ይቅር ያሉት ብጹዕ አቡነ ፊሊጶስ በብጹአን … Continue reading

More Galleries | 20 Comments

የብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ወደ አሜሪካን መመደብ ተቃውሞ ለምን አስፈለገ???

This gallery contains 1 photo.

ከአሐቲ ተዋሕዶ የተወሰደ        ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ እንደዘገብነው በሰሜን አሜሪካ ለቤተ ክርስቲያን ክፍፍል ዋናኛው ተዋናኝ ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ነበሩ:: ብፁዕነታቸ የጵጵስና ማዕረግ ከማግኘታቸው በፊት “አባ መላኩ” በመባል ይጠሩ ነበረ:: በወቅቱም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰሜን አሜሪካ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ … Continue reading

More Galleries | 10 Comments

የፓትርያርክ ጳውሎስ ቁማርና የቤተክርስቲያን ተስፋ

This gallery contains 1 photo.

በቀሲስ ኢ/ር ወንድምስሻ አየለ( Wendemsesha Ayele Kesis )           ቁማር ከመዝናናት ሌላ ጥቅም ለማግኘት ሲባል የሚጫወቱት ሕጋዊና ሕገወጥ ጫወታ መሆኑና ማንኛውንም ጫወታ በቁማርነትም ሆነ በመዝናኛነት ለይቶ የመጫወቱ ድርሻ የተጫዋቹ መሆኑ ግልጥ ነው፤ ካርታን ለመዝናኛነትም፣ ሲያስፈልግ ደግሞ በሕገወጡ ቁማርነትም መጫወት … Continue reading

More Galleries | 10 Comments

የአቡበከርን ልጅ ሳየው አናደደኝ

ገብርኄሮች ሰሞኑን ስለተለቀቀው ቪሲዲ በሰጣችሁት መረጃ መሠረት አዲስ አበባ ካለው የሰ/ትቤት ወዳጄ ሲዲውን ወስጄ አየሁት፡፡ በረካቶችን የእናት ጡት ነካሾች አየሁ፡፡ በጣም የገረመኝ ግን ሰሎሞን አቡበከር የተባለው ሰው ነው፡፡         ሰሎሞን አቡበከር መተሃራ አካባቢ ተውልዶ ያደገ ከእስልምና ዕምነት … Continue reading

More Galleries | 12 Comments

እውነታው ምንድን ነው? (ዘእግዚእነ ዘዋርካ)

አንድ አስተያየት ሰጭ የራሱን ሃሳብ በብእር ስም ልኮልን አንባቢያን አስተያየት እንድሰጡበት እንዳለ አውጥተነዋል መልካም ንባብ፡፡ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን! የዚህ ጽሑፍ ዓላማ እኛ ኦርቶዶክሳዊያን ክርስቲያኖች ከግርግር ይልቅ በውውይት በዳበረ እና ጥናታዊ በሆነ መልኩ ያሉንን መልካም ጎኖችና … Continue reading

More Galleries | 46 Comments

ሦስት መቶ ሺህ ተሽጦ ሰባ ሺህ ጉርሻ ያስገኘ…..

This gallery contains 2 photos.

          ተካ ፍሬሰንበት ከራጉኤል መርካቶ  የአዲስ አበባ ሰ/ት/ቤት ወጣቶች ከተሐድሶ መናፍቃን ጋር የሚያደርጉት ግብግብ ተሳክቶ ፍሬ እያስገኘ ነው፡፡ ምዕመኑም “ከልጆቻችን ይልቅ ለቤተ ክርስቲያን የቀረበ የለም የምንሰማው እነሱን ነው” ብሎ እየተከተላቸው ነው፡፡ ይኽ በእውነት ትልቅ ለውጥ ነው፡፡ አሁንም ቢሆን የሰንበት ት/ቤት … Continue reading

More Galleries | 17 Comments

“የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ አከብራለሁ፣ የተመደብኩበት ቦታ እሄዳለሁ” ብፁዕ አቡነ አብረሃም

This gallery contains 1 photo.

ከአሐቲ ተዋሕዶ የተወሰደ ዛሬ በሲልቨር እስፕሪንግ ሜሪላድ ኆኅተ ምሥራቅ ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን የቅዳሴ ቤት ለማክበር የተገኙት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብረሃም ወደ ኢትዮጵያ ቅዱስ ሲኖዶስ ወደ መደባቸ ሀገረ ስብከት … Continue reading

More Galleries | 13 Comments

ሰበር ዜና ፡- በጋሻው ደሳለኝ በመምህር ደስታ እና መምህር ዘመድኩን ላይ ያቀረበው ክስ እንዲቋረጥ ትዕዛዝ ተሰጠ፡፡

በሜቲ ኤጄታ (memettiej1@gmail.com) ብጹዕ አቡነ ፊሊጶስ ጉዳዩ ሃይማኖታዊ በመሆኑ መዝገቡ እንዲቋረጥ ጠይቀዋል፡፡ በጋሻው ደሳለኝ በጻፏቸው መጻሕፍት እና በሰጧቸው ቃለ መጠይቆች ስሜን በማጥፋት ከህዝብ ልብ እንድወጣ አድርገውኛል በማለት ያቀረበው ክስ የፍርድ ቤት ሂደቱ ሳይጠናቀቅ መዝገቡ ተቋርጦ ለምርመራ እንዲላክ ትዕዛዝ ተሰጥቶበታል፡፡  መምህር … Continue reading

More Galleries | 28 Comments

እውነታው ምንድን ነው? (ዘእግዚእነ ዘዋርካ)

ክፍል ሁለት በቤተ ክርስቲያን የትኛው ተሃድሶ ያስፈልግ ይሆን? ባለፈው ጽሑፋችን ስለማህበረ ቅዱሳን መልካምና ደካማ ጎኖች ስለተሃድሶዎችና ፍላጎታቸው ተመልክተናል:: በተለይም ደግሞ ተሃድሶዎች ከእምነታቸው አንጻር ፕሮቴስታንትና ኦርቶዶክስ ተብለው እንደሚከፈሉ:: ፕሮቴስታንት ተሃድሶዎች ግባቸው ተዋህዶን ወደ ፕሮቴስታንትነት መቀየር ሲሆን ካልቻሉ ደግሞ ምእመናንን መንጠቅና ወደ … Continue reading

More Galleries | 17 Comments

በወንጌል አላፍርም ሮሜ ፩፦፲፮

በዶ/ር አባ ኃይለ ማርያም መለሰ በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክን የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልዕኮ መምሪያ ኃላፊ        የሲኖዶሱን  የስብሰባ ሂደት ለመከታተል ጠቅላይ ቤተክህነት ግቢ ውስጥ ባለች አንድ  ሻይ ቤት ቁጭ ብያለሁ፡፡ አንድ አባት ቀጥሎ የማስነብባችሁን ጥናታዊ ጽሑፍ በመያዝ  ፊታቸውን ሲያራግቡበት ባይ ርዕሱ  ሳበኝ ና … Continue reading

More Galleries | 8 Comments

እውነታው ምንድን ነው? (ዘእግዚእነ ዘዋርካ christtewahedo@gmail.com)

ክፍል ሦስት         ኦርቶዶክስ ተሃድሶዎች በአንደኛ ደረጃ ያስቀመጥናቸው ኦርቶዶክስ ተሃድሶዎች በኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ዶግማ የሚያምኑ ሲኖዶሱ ቀኖና ማውጣት እንደሚችል ቀኖናውን መቀበልና ማክበር እንደሚገባ የሚያምኑ ናቸው:: ሆኖም ግን በአንዳንድ ጉዳዮች ቤተ ክርስቲያን ስር ነቀል ለውጥ ማድረግ አለባት በለው ለውጥ የሚናፍቁ ናቸው:: … Continue reading

More Galleries | 43 Comments

የድሬዳዋ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ውዝግብ ቀጥሏል

This gallery contains 1 photo.

በያሬድ ይስማሸዋ (yismayared21@gmail.com)  ምእመናን ኦዲቱን እኛ በመረጥናቸው መደረግ አለበት እያሉ ነው ሰበካ ጉባኤው ከተሰበሰበ 6 ወር አልፎታል ለዚህ ሁሉ ተጠያቂው አለቃው ናቸው የህንጻ አሰሪው ሊቀመንበር ህዝብ ካልፈለገኝ እለቃለሁ ሲል ህዝቡ በጭብጨባ ሸኝቶታል በድሬዳዋ ከተማ በሚገኘው የደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተ … Continue reading

More Galleries | 16 Comments

የአቡነ ገሪማ አምላክ አባ ጳውሎስ ይሆኑ?

በሉልሰገድ እረታ lulsegedrt@gmail.com           ክርስትና የመከራ ህይወት ነው እንደሚባለው ሆኖ እንደሆነ እንጃ በየትኛውም ዘመን የተፃፈ የትኛውንም የታሪክ መጽሐፍ የተመለከተ ሰው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ከፈተና እና ከመከራ የተላቀቀችበት ዘመን እንደሌለ በቀላሉ መረዳት ይችላል፡፡ በ10ኛው መቶ ክ/ዘመን የዮዲት ወረራ፣ በ16ተኛው ክ/ዘመን … Continue reading

More Galleries | 21 Comments

በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚካሄዱ ግንባታዎች ከፍተኛ የሙስና ምንጭ እየሆኑ ነው (ከአማናዊቷ ደጀ ሰላም የተወሰደ)

       አርእስተ ነጥቦች (ደጀ ሰላም፣ ታኅሣሥ 6/2004 ዓ.ም፤ ዲሴምበር 16/2011)፦ ለድሬዳዋ ደብረ ኀይል ቅዱስ ገብርኤል ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ግንባታ ከጅምሩ አንሥቶ በሀገር ውስጥና በውጭ ከሚገኙ ምእመናን ከተሰበሰበው ብር 11.3 ሚሊዮን ውስጥ ከአምስት ሚሊዮን ብር በላይ ጉድለት መገኘቱን በምእመናን ምርጫ የተዋቀረው … Continue reading

More Galleries | 2 Comments

የድሬዳዋ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ውዝግብ ቀጥሏል…

This gallery contains 1 photo.

በሸዊት ገ/ኪዳን (shewitgbrkdn95@gmail.com) v የሰበካ ጉባኤው አባላት ሥርዓተ ቤተክርስቲያን ጥሰዋል ከግቢ መውጣት አለባቸው፡፡ አቡነ ገሪማ v  ስለ ቤተክርስቲያን ገንዘብ መውጣት ምዕመን ምን አገባው ሲጠየቅ መስጠት እንጂ፡፡ አቡነ ጳውሎስ v  ስሜ ስለጠፋ ከአሁን በኋላ አልሰራም፡፡ ኮንትራክተሩ v  እኛን መቀየር ማባረር አይደልም … Continue reading

More Galleries | 8 Comments

አቡነ ገሪማ ኃላፊነት በጎደለው መልኩ የጻፏቸው ሁለት ደብዳቤዎች ህዝቡን እያሳዘነ ነው፡፡

This gallery contains 1 photo.

በሸዊት ገብረ ኪዳን(shewitgbrkdn95@gmail.com ) እስከ አሁን ከመናፍቃን ቤት ያልተመለሰን እነ «ዲ/ን» ቤዛን ይመለሱ ደሞዝም ባስቸኳይ እንዲከፈል ብለዋል፡፡ ህንፃው የዘገየው በህንፃ አሰሪው ችግር ሳይሆን በቤተክርስቲያን ችግር ነው ብለው ጻፉለት፡፡ ሲውዛገብ የቆየው የቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ሕዝብ አቡነ ገሪማን ባዶ ያስቀረ ምርጫ አካሂዷል፡፡ … Continue reading

More Galleries | 6 Comments

የዛፍ ላይ እንቅልፍ

Mulualem Tamire Sheferaw 7:01pm Dec ማክሰኞ፣ ታሕሣሥ 17/2004 ዓ.ም. በአገራችን ምስራቃዊ ክፍል ከሚገኙ ከተሞች መካከል በአንዱ ጆሮዬ የሰማውና ልቤ የታዘበው ነገር ለዚህ ጽሑፍ መዘጋጀት በምክንያትነት አገልግሏል፡፡ ባለሥልጣን የነበረ አንድ ሰው (የዛሬን አያድርገውና) ዓይንን ከሚያማልል አካባቢው፣ ለኑሮ ምቹ ከሆነ ቤቱ፣ ደኅንነቱን … Continue reading

More Galleries | 1 Comment

የድሬዳዋ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን መዝባሪዎች እጃቸውን ከደብሩ እና ከሀገረ ስብከቱ ላይ እንዲያነሡ ተጠየቀ

  • የደብሩ አስተዳዳሪ የአጥቢያውን ልማት የመምራት አቅም የላቸውም::
  • ፖሊስ ሁለት የሰንበት ት/ቤት ወጣቶችንና አንድ ምእመን ይዞ አስሯል::
  • ተዋንያኑ ፋንቱ ማንዶዬ እና ችሮታው ከልካይ በቁሉቢ ለአኵስም ጽዮን ሙዚዬም ግንባታ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር ያካሂዳሉ::
 (ከእውነተኛዋ ደጀ ሰላም፣ ታኅሣሥ 18/2004 ዓ.ም፤ ዲሴምበር 28/2011. READ IN PDF)፦ በድሬዳዋ ሀገረ ስብከት የሚገኙ የስምንት አጥቢያ አብያተ ክርስቲያን ሰንበት ት/ቤቶች ወጣቶች እናምእመናን በሳባ ደብረ ኀይል ቅዱስ ገብርኤል ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ግንባታ የተፈጸመው ሙስና ተጣርቶ በሙሰኞቹ ላይ ሕጋዊ ርምጃ እንዲወሰድ፣የደብሩን አስተዳደር በመምራት ረገድ የከፋ የአቅም ማነስታይቶባቸዋል፤በሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤው የተተለሙ የልማት ዕቅዶች ተፈጻሚ እንዳይሆኑ ዕንቅፋት ፈጥረዋልየተባሉት የደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ ኀይል ቆሞስ አባ ገብረ እግዚአብሔር ቸኮል ከሓላፊነታቸው እንዲወገዱ በተቃውሞ ትዕይንት ጠየቁ፡፡
የተቃውሞ ተሰላፊዎቹ “ደካማ እና ነውረኛ” በማለት ለገለጧቸው የደብሩ አስተዳዳሪ እና ለሙሰኞቹ የሕንፃ አሠሪ ኮሚቴ አመራሮች ሽፋን በመስጠት ዝርፊያውን አጠናክረዋል፤ ምእመኑ በየደረጃው ላቀረባቸው አቤቱታዎች በአድርብዬ ጠባይ ተመጣጣኝ ርምጃ አልወሰዱም ያሏቸውን የሀገረ ስብከቱን ሥራ አስኪያጅም ነቅፈዋል፡፡ የከተማው ፖሊስ ኮሚሽን የተቃውሞ ትዕይንቱን ቀስቅሰዋል፤በዋናነትም አስተባብረዋል ያላቸውን ሁለት የሳባ ደ/ኀ/ቅ/ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ት/ቤት ወጣቶች እና አንድ ምእመን ይዞ ማሰሩም ተመልክቷል፡፡ ሁለቱ ወጣቶች እና ምእመኑ በድሬዳዋ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ቀርበው ምርመራዬን አልጨረስኩም ባለው ፖሊስ የ14 ቀናት ጊዜ ቀጠሮ የተጠየቀባቸው ቢሆንም ፍ/ቤቱ ከአራት ቀናት በኋላ እንዲያቀርባቸው ትእዛዝ ሰጥቷል፡፡
የሰንበት ት/ቤት ወጣቶቹ እና ምእመናኑ ጥያቄዎቻቸውን በተቃውሞ ትዕይንት ያቀረቡት በየዓመቱ ታኅሣሥ 19 ቀን በርእሰ አድባራት ቁሉቢ ደብረ ፀሐይ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ከሚከበረው የቅዱስ ገብርኤል ክብረ በዓል አስቀድሞ ዛሬ ረፋድ ላይ ወደ ድሬዳዋ ላመሩት ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ የተለመደው አቀባበል በሚደረግበት በደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል በመገኘት ነው፡፡ ወጣቶቹ እና ምእመናኑ ጥያቄያቸውን ለፓትርያርኩ ለማቅረብ በካቴድራሉ ተሰልፈው በሚጠባበቁበት ወቅት በመፈክር መልክ ከያዟቸው ኀይለ ቃሎች ውስጥ፡- “የሳ/ደ/ኀ/ቅ/ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ብቃት ስለሚያንሣቸው ከሓላፊነታቸው ይነሡ”፤ “እነ ኢንጅነር ሰሎሞን ካሳዬ ከሀገረ ስብከታችን ላይ እጃቸውን ያንሡ”፤ “የብፁዓን አባቶቻችንን ውሳኔ እናከብራለን” የሚሉ ይገኙበታል፡፡

ፓትርያርኩ ቀትር ላይ ድሬዳዋ አየር ማረፊያ ሲደርሱም ሆነ በካቴድራሉ ከተገኙ በኋላ ለወትሮው አቀባበሉን የሚያደምቁት የሀገረ ስብከቱ ስምንት አጥቢያ አብያተ ክርስቲያን አስተዳዳሪዎች፣ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤያቱ ሊቃነ መናብርት፣ የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች እና ምእመናን እንደ ወትሮው አለመገኘታቸው ታውቋል፡፡ ለፓትርያርኩ አቀባበል መቀዝቀዝ የወዲያው ምክንያቱ ፖሊስ በሰላማዊ መንገድ ጥያቄያቸውን ለማቅረብ ከተዘጋጁት ወጣቶች መካከል ሁለቱን፣ ከምእመናኑም አንዱን ለይቶ በመውሰዱ ሰልፈኞቹ ወደታሰሩበት ፖሊስ ጣቢያ በመሄዳቸው ነው ተብሏል፡፡ ዓይነተኛው ምክንያት ደግሞ በሳባ ደብረ ኀይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ሕንፃ ሥራ ጋራ በተያያዘ የተፈጸመው ሙስና እና በተሐድሶ ኑፋቄ አራማጅነታቸው የተነሣ ውሳኔ የተላለፈባቸውን ሦስት ግለሰቦች ቀኖናዊ ቅጣት አፈጻጸም ቸል በማለት የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ እና ሊቀ ጳጳስ ወደ ቀድሞ ቦታቸው እንዲመለሱና በእግዳቸው ወቅት ‹የቆያቸው› ውዝፍ ደመወዛቸው እንዲከፈላቸው ትእዛዝ ማስተላለፋቸው፣ ይህን ውሳኔያቸውን እንዲያጤኑ ለቀረበው ጥያቄም ምላሽ አለመስጠታቸው በአገልጋዩ እና ምእመኑ ዘንድ የፈጠረው ቁጣና ሐዘን መሆኑ ተዘግቧል፡፡

ለእስር ከተዳረጉት ሁለት ወጣቶች መካከል አንዱ (ኢንጅነር ወንድወሰን ብርሃኑ) ለሕንፃ ቤተ ክርስቲያኑ ሥራ በአማካሪ መሐንዲስነት ያገለገለ እና በዋናነት በኮሚቴው ሰብሳቢ ብርሃኔ መሐሪ የሚፈጸመውን ሙስና ሲቃወም የቆየ ነው፤ የእስሩ ዓላማ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ምሕንድስና ዘርፍ ሓላፊ አቶ ሰሎሞን ካሳዬ ታኅሣሥ 19 ቀን በደብሩ ሕንፃ አሠሪ ኮሚቴ የተፈጸመውንና እርሳቸውም ከጥቅሙ ተጋሪ የሆኑበትን የጠቅላይ ቤተ ክህነቱን የኦዲት ሪፖርት የሚያስተባብል የማስተባባያ ሪፖርት ያለ ተቃዋሚ ለምእመኑ ለማቅረብ ለማስፈራራት የታቀደ ሳይሆን እንደማይቀር ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው አካላት ተናግረዋል፡፡ ቀደም ሲል አቶ ሰሎሞን በተመሳሳይ መንገድ ያደረጉት የተሳሳተ የማስተባባያ ሪፖርት የማቅረብ ሐሳብ በምእመኑ ማስጠንቀቂያ የከሸፈ በመሆኑ ለነገው ክብረ በዓል የተዘጋጁበት ሙከራም እንደማይሳካላቸው ምእመናኑ እየተናገሩ ይገኛሉ፡፡
የጠቅላይ ቤተ ክህነት ቁጥጥር አገልግሎት ኦዲተሮች ከሳባ ደብረ ኀይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ሕንፃ አሠሪ ኮሚቴ አመራሮች እስከ መንበረ ፓትርያርኩ በተዘረጋው የጥቅም ሰንሰለት ስለተፈጸመው ሙስና አጣርተው ባቀረቡት ሪፖርት መሠረት ከፕሮጀክት አማካሪ መሐንዲስ ይሁንታ ሳይገኝ፣ ምንም ዓይነት የቅድመ ክፍያ ዋስትና ሳይቀርብ አላግባብ ለሕንፃ ሥራ ተቋራጩ ከፍተኛ ገንዘብ ተከፍሏል፡፡
በቃል ትእዛዝ እና ያለዋስትና በብድር መልክ ለሕንፃ ሥራ ተቋራጩ በየጊዜው የተፈጸመው ይኸው ያልተገባ ክፍያ በውለታ ጊዜው ውስጥ ለሕንፃው አጠቃላይ የግንባታ ፕሮጀክት ሊከፈል ከነበረው ወጪ ከግማሽ በላይ ነው፡፡ ሆኖም የሕንፃ ሥራው ከውል ጊዜው አራት ዓመት በላይ ዘግይቶም ከ65 በመቶ በላይ ባለመጠናቀቁ፣ ይህም በየጊዜው በሚንረው የግንባታ ማቴሪያሎች ወጪ የተነሣ ሕንፃው መጀመሪያ ከተገመተው 2.9 ሚሊዮን ብር ጠቅላላ ወጭ ወደ 4.8 ሚሊዮን ብር በማሻቀቡ ደብሩን ለከፍተኛ ወጪ እየዳረገው እንደሚገኝ ተመልክቷል፡፡ ከዚህም ባሻገር ከሕንፃው ዲዛየን ጋራ የማይጣጣሙ በግንባታው ገጽታ ላይ የሚስተዋሉ የኢንጂነሪንግ ችግሮች መኖራቸውም ነው የሚነገረው፡፡
የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የቁጥጥር አገልግሎት ኦዲተሮች በምርመራ ስላረጋገጡት የ1.8 ሚሊዮን ብር ጉድለት መተማመን ተፈጥሮ የደብሩ ሰበካ አስተዳደር ጉባኤ በጉድለቱ ሳቢያ በሕንፃ ሥራ ተቋራጩ ቀጣይነት እንዲሁም በተጓተተው ግንባታ ዕጣ ፈንታ ላይ ያነሣቸው ጥያቄዎች መፍትሔ ሳይበጅላቸው የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ምሕንድስና ዘርፍ ኢንጅነር ሰሎሞን ካሳዬ ከፓትርያርኩ ልዩ ጸሐፊ እና ከሕንፃ አሠሪው ኮሚቴ ሰብሳቢ ብርሃኔ መሐሪ ጋራ በመተባበር የኦዲተሮችን አቋም የሚያስቀይር እና የቀደመውን ኦዲት ሪፖርት ግኝቶች የሚያስተባብል የቅሰጣ ሪፖርት በጓሮ በር አዘጋጅተዋል፡፡ በዚህም ሳያበቁ ከምእመኑ እና ከመንግሥት ተጠያቂነት በመሸሽ ከሀገር ጠፍቶ ለሰነበተው የሕንፃ ሥራ ተቋራጭ ከውል ጊዜው ውጭ ለሆነና በ1994 ዓ.ም የቋሚ ኮንስትራክሽን መተዳደሪያ ደንብ አንቀጽ 70 መሠረት ዝርዝሩ ተለይቶ ላልታወቀ የግሽበት/የግንባታዋጋ መናር በሚል የተጨማሪ ብር 900,000 ክፍያ እንዲፈጸም አጸድቀዋል፤ እንደ ምንጮቹ ጥቆማም ከዚህ ሕገ ወጥ ክፍያ እንደ የደረጃቸው ጥቅም ተጋርተዋል፡፡
የኤጲስ ቆጶስ ሹመት ተስፈኛው የሆኑት የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ ቆሞስ አባ አረጋዊ ነቦምሳ እና የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ገሪማ ለዚህ ሁሉ በደል ቸልተኝነት በማሳየት የተፈጸመውን ሙስና እና የአስተዳደር በደል ለመረጠው ምእመን በሪፖርት አጋልጦ የተተኪ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ አባላትን ለማስመረጥ የተዘጋጀውን ሰበካ ጉባኤ አስተዳደር አባላት ከቃለ ዐዋዲው ውጪ ከሓላፊነታቸው እንዲለቁ ከፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት በተጻፈ ደብዳቤ መመሪያ እንዲወርድ አድርገዋል፡፡
ይሁንና ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተለው የአጥቢያው ምእመን ከትላንት በስቲያ እሑድ በተካሄደው አዲስ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ አባላት ምርጫ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ በሐቅ የሚያገለግሉትን የቤተ ክርስቲያን ልጆች መርጧል፡፡በአንጻሩ ብርሃኔ መሐሪ የተባሉ የሕንፃ አሠሪ ኮሚቴው ሰብሳቢ ግን ከሌሎች የጥቅም ተጋሪዎቻቸው ጋራ አሁንም በሓላፊነታቸው ላይ እንደተቀመጡ ይገኛሉ፡፡ዛሬ የከተማው ምእመናን እና የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች ጥያቄያቸውን በሰላማዊ መንገድ ለማቅረብ በተዘጋጁበት ሁኔታ ለሁለት ወጣቶች እና አንድ ምእመን መታሰር የእኚህ ግለሰብ ግፊት እንዳለበት ተጠቁሟል፡፡ግለሰቡ በስመ ታጋይ የሚነግዱ፣ የድሬዳዋ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዐቃቤ ነዋይ በነበሩበት ወቅት የፌዴሬሽኑን ካዝና በማራቆት የተባረሩ፣ ከደብሩ ሕንፃ ግንባታ ፕሮጀክት በሚጋሩት ሕገ ወጥ ጥቅም ሽንሌ በተባለ የከተማዋ ክፍል የግል ኢንቨስትመታቸውን እያካሄዱ የሚገኙ ሙሰኛ እና ጀብደኛ ግለሰብ መሆናቸው ይነገርባቸዋል፡፡
ብፁዕ አቡነ ገሪማ የፌዴራዊ መንግሥት ሁለተኛ ከተማ የሆነችው ድሬዳዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ይሁኑ እንጂ በመንበረ ጵጵስናቸው አሉ ለማለት እንደማያስደፍር የሀገረ ስብከቱ ምንጮች ይናገራሉ፡፡ “የሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት ሠራተኞች ደመወዝ የሚከፈለው የሒሳብና በጀት ክፍል ሠራተኛው በየወሩ አበል እየታሰበለት ደመወዝ መክፈያ ቅጽ እየያዘ አዲስ አበባ ጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ ድረስ እየተመላለሰ ብፁዕነታቸውን በማስፈርም ነው፤” ይላሉ በሊቀ ጳጳሱ ግራ የተጋቡ አስተያየት ሰጪዎች፡፡ ይሁንና አስተያየት ሰጪዎቹ እንደሚናገሩት እንኳን አሁንና ቀድሞም አቡነ ጳውሎስ በዓመት ሁለት ጊዜ፣ ታኅሣሥ 19 እና ሐምሌ 19፣ ለቅዱስ ገብርኤል ክብረ በዓልወደ ድሬዳዋ በወረዱ ቁጥር ሊቀ ጳጳሱ አይለዩዋቸውም፡፡ ዛሬም ፓትርያርኩ ወደ ድሬዳዋ ሲያመሩ ከብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል፣ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ እና ብፁዕ አቡነ ያሬድ ጋራ ብፁዕ አቡነ ገሪማም አብረዋቸው ነበሩ፡፡ በእነዚህ የፓትርያርኩ ምልልሶች ወቅት የሀገረ ስብከቱ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያን ተራ ገብተው ለእያንዳንዱ አቀባበል በፉክክር መልክ ለመስተንግዶ በሚያወጡት በርካታ ሺሕ ብሮች(በትንሹ ከ20,000 ብር ያላነሰ) ግብር ያስገባሉ፡፡
ዛሬ ማምሻውን ፓትርያርኩ በ1.5 ሚሊዮን ብር ያሠሩት ማረፊያቸው በሚገኝበት በደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ከወትሮው ያነሰ ቁጥር ያለው ምእመን በተገኘበት የሠርክ መርሐ ግብር ተካሂዷል፤ አቡነ ጳውሎስም ነገ ታኅሣሥ 18 እና 19 ቀን በቁሉቢ ደ/ፀ/ቅ/ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን በመገኘት ለአኵስም ጽዮን ቤተ መጻሕፍት ወመዘክር(ሙዚዬም) ማሠሪያ የገቢ ማሰባሰቢያ ቅስቀሳ ያካሂዳሉ ያሏቸውን ተዋንያን ፋንቱ ማንዶዬንና ችሮታው ከልካይን አስተዋውቀዋል፡፡ከእነርሱም ጋራ የካህናት አስተዳደር መምሪያ ሓላፊ(መጋቤ ካህናቱ) ሊቀ ማእምራን ኀይለ ሥላሴ ዘማርያም፣ ጌታቸው ዶኒ እና ሌሎችም ግለሰቦች መኖራቸው ተዘግቧል፡፡
በቀደመው ዜና ዘገባችን እንደገለጽነው የርእሰ አድባራት ቁሉቢ ደብረ ፀሐይ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን በክብረ በዓል በሚያስገኘው በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ፣በስእለት እና መባዕ በሚገቡት ስፍር ቁጥር የሌላቸው ንዋያተ ቅድሳት አማካይነት በተቋቋመው “የቁሉቢ ንዋያተ ቅድሳት ማደራጃ”ለአህጉረ ስብከት፣ ተቋማት እና መንፈሳዊ ኮሌጆች ድጎማ በሚል ሀብቱ በየጊዜው ወደ መንበረ ፓትርያርኩ ቢጋዝም ደብሩ እና አካባቢው ግን ከአንድ መለስተኛ ት/ቤት በቀር የተሠሩለት የልማት ተግባራት የሉትም፡፡
Posted in ሐተታ | 2 Comments

ሰበር ዜና – ቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ስብሰባ አካሄደ !!

(ከአማናዊቷ ደጀ ሰላም የተወሰደ!!!) በየአህጉረ ስብከቱ ለሚፈጠሩት ችግሮች የአቡነ ጳውሎስ ግፊት እንዳለበት ቅዱስ ሲኖዶስ ገለጸ። አስቸኳይና ድንገተኛ ስብሰባ የተጠራው የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ፓትርያርኩ ያቀረቧቸው አጀንዳዎች “ለአስቸኳይ ስብሰባ የማይበቁ ናቸው” በሚል አጣጥሏቸዋል:: በፓትርያርኩ እልከኝነትና ተንኮል ላይ ያመረሩት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት “የቤቱ … Continue reading

More Galleries | 5 Comments

የጌታችን ልደት!!

This gallery contains 2 photos.

እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት በሰላም አደረሳችሁ!!

More Galleries | Leave a comment

የአራዳው ፍ/ቤት መ/ር ዘመድኩን እንዲከላከል አዘዘ

ከደጀ ሰላም የተወሰደ READ THIS ARTICLE IN PDF. በእናቱ ሞት በደረሰበት ኀዘን እና በቁሉቢ ጉዞ በአራዳው ምድብ ችሎት በቀጠሮ ያልተገኘው መ/ር ዘመድኩን “የመደመጥ መብቴ ተነፍጓል፤ ከውሳኔ አስቀድሞ አቋም ተይዞብኛል” በማለት በዳኛው ላይ ምሬቱን ገልጧል:: “እናቱ ለመሞታቸው የሕክምና ማስረጃው ተተርጉሞ ይቅረብ፤ … Continue reading

More Galleries | Leave a comment

የአዲሱ ሚካኤል ካቴድራል ምእመናን አስተዳዳሪውን አገዱ!!!!

(ፍትሕ ጋዜጣ ቅጽ 5 ቁጥር 173 አርብ ጥር 25 2004 ዓ.ም) ‹‹አቡነ ጳውሎስ እና የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ቃላቸውን አልጠበቁም›› …. ምእመናን አስተዳዳሪው ቀደም ሲል የደብረ ጽጌ ቅዱስ ዑራኤል ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ በነበሩበት ወቅት እስከ 500 ሺህ ብር መዝብረው በፌዴራል የመጀመሪያ … Continue reading

More Galleries | Leave a comment

ሰበር ዜና፡- የጎንደር መድኃኔዓለም ጉባዔ ቤት የእሳት ቃጠሎ አደጋ ደረሰበት!!

This gallery contains 1 photo.

ትላንት ማምሻውን በግምት ከቀኑ 11፡00 ሲኖን የጎንደር መዲኃኔዓለም ጉባዔ ቤት የአሳት ቃጠሎ አደጋ እንደደረሰበት ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመልክቷል፡፡ በቃጠሎው አደጋ የደረሰበት የጉባዔ ቤቱ ክፍል የደቀመዛሙርት ማረፊያ ነው፡፡ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ጥንታዊ የብራና መጻሕፍት፣ የደቀመዛሙርት  ማረፊያ እና ቀለብ በቃጠሎው ከፍተኛ ጉዳት … Continue reading

More Galleries | Leave a comment

በቅዱስ ሲኖዶስና በስደት በሚገኙት አባቶች መካከል የዕርቀ ሰላም ውይይት እየተካሄደ ነው

ከደጀ ሰላም የተወሰደ         ከአገር ቤት ልዑካን አንዱ የሆኑት ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ ከጤና እክል ጋራ በተያያዘ በውይይቱ ላይ አይሳተፉም፤ ወደ ቅዱስ ገብርኤል ሆስፒታል ገብተው ሕክምና እየተከታተሉ ነው። (ደጀ ሰላም፣ የካቲት 7/2004 ዓ.ም፤ ፌብሩዋሪ 15/2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ … Continue reading

More Galleries | Leave a comment

በጎንደር ከተማ ሁለት የአብነት ት/ቤቶች ሙሉ በሙሉ ተቃጠሉ !!! (ደጀ ስላም)

አንዱ ቤተ ጉባኤ በኢትዮጵያ ብቸኛው የመጻሕፍተ መነኮሳት ትርጓሜ ማኼጃ ነበር ተብሏል:: (ደጀ ሰላም፤ የካቲት 8/2004 ዓ.ም፤ ፌብሩዋሪ 16/2012)፦ በሰሜን ጎንደር ሀ/ስብከት ጎንደር ከተማ በሳምንት ልዩነት በሁለት አጥቢያ አብያተ ክርስቲያን በተነሡ የእሳት ቃጠሎ አደጋዎች አንድ ጥንታዊ የመጻሕፍት ትርጓሜ ቤት ሌላ የቅኔ … Continue reading

More Galleries | Leave a comment

ጌታቸው ዶኒ እንደገና ወደ ዜና ብቅ ሲል

(ከአማናዊቷ ደጀ ሰላም) ዳግመኛ በተሾመበት ደብር የተቀሰቀሰው የምእመናን ተቃውሞ ተጠናክሯል።   የደብሩ ሰንበት ት/ቤት ወጣቶች እስርና ማስፈራሪያ እየተፈጸመባቸው ነው። (ደጀ ሰላም፣ የካቲት 21/2004 ዓ.ም፤ ፌብሩዋሪ 29/2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ በግንቦት 2003 ዓ.ም የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ራሳቸውን “ወንጌላውያን” … Continue reading

More Galleries | Leave a comment

ሰበር ዜና፡ በአሰቦት ደብረ ወገግ አቡነ ሳሙኤል ገዳም የእሳት ቃጠሎ ተነሳ!!!

የእሳት ቃጠሎው እንደቀጠለ ነው፡፡ እስካሁን እሳቱን ለማጥፋት የተወሰደ እርምጃ የለም፡፡ ቃጠሎው ሊነሳ የቻለው በተኩስ ልውውጥ ነው፡፡ (ሜቲ ኤጀታ memettiej1@gmail.com) በአሰቦት ደብረ ወገግ አቡነ ሳሙኤል ገዳም የእሳት ቃጠሎ አደጋ መከሰቱን የአከባቢው ምንጮች ገለጹ፡፡ እንደ ደረሰን መረጃ ከሆነ የእሳት ቃጠሎው ሊከሰት የቻለው … Continue reading

More Galleries | Leave a comment

ሰበር ዜና ፡- ፍርድ ቤቱ መ/ር ደስታ ላይ የጥፋተኝነት ብይን ሰጠ፡፡

በሜቲ ኤጄታ (memettiej1@gmail.com) ‹‹የሰባኪው ሕጸጽ›› በተሰኘው መጽሐፉ የስም ማጥፋት ወንጀል ፈጽሞብኛል በማለት በጋሻው ደሳለኝ ባቀረበበት ክስ ክርክር ሲያደርግ የቆየው መ/ር ደስታ ዛሬ ረፋድ ላይ በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቦሌ ምድብ ችሎት ጥፋተኛ ተብሏል፡፡ እንደ መ/ር ደስታ አስተያየት ከሆነ ፍርድ … Continue reading

More Galleries | Leave a comment

ሰበር ዜና፡- በደብረ ወገግ አሰቦት ገዳም ዳግም የእሳት ቃጠሎ ተነሳ!!!

መነኮሳቱ እሳቱን መቆጣጠር ባለመቻላቸው ከአባ ሳሙኤል ቤተ ክርስቲያን ወደ ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ሸሽተዋል፡፡ ገዳሙ ላይ በተደጋጋሚ እየደረሰ ባለው ጉዳት የገዳሙ ባለቤት የሆነችው ቤተክርስቲያን እንደተቋም አንዳችም እርምጃ አለመውሰዷ የሚያሳዝን ነው፡፡ (ታዛቢዎች) በሜቲ ኤጀታ (memettiej1@gmail.com) የካቲት 20 ቀን 2004 ዓ.ም ለሦስተኛ … Continue reading

More Galleries | Leave a comment

የሰከነ ልቡና የሚሻው የዋልድባ ገዳማት ህልውና እና የመንግስት የልማት እንቅስቃሴ!!!!

በያሬድ ይስማሸዋ (yared_yisma@yahoo.com) የኢፌዲሪ መንግስት በዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ ሊያለማቸው ካቀዳቸው አስር የስኳር ፋብሪካዎች አንዱ ነው በወልቃይት ወረዳ በ4.2 ቢሊዮን ብር የሚገነባው ፍብሪካ፡፡ የፋብሪካው ግንባታ በዋልድባ በሚገኙ ሦስት ገዳማት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ያሳርፋል ገፋም ሲል ህልውናቸው ያጠፋል በሚል በተለየዩ መገናኛ ብዙሃን … Continue reading

More Galleries | Leave a comment

ራእየ ዮሐንስ…” ለበይነ ዲሲፕሊናዊ ንባብ የሚየተጋ መጽሐፍ

አዲስ አድማስ ጋዜጣ ከገዛኸኝ ፀ.  ዳንኤል ክብረት የተፈተነበት፣ አንባቢ የሚፈተንበት ጥንቁቅ ሥራ… በተለያዩ ሃይማኖታዊ ፍልስፍናዎችና የሥነ እውቀት ንድፈ ሃሳቦች የሚዳኝ መጽሐፍ…  ፈር መያዣ:- የዚህ ጽሑፍ ዓላማ፣ “ራእየ ዮሐንስ – የዓለም መጨረሻ” በሚል ርዕስ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት በቅርቡ ለንባብ ባበቃው መጽሐፍ … Continue reading

More Galleries | Leave a comment

ሰበር ዜና፡- ፍርድ ቤቱ መ/ር ደስታን በገደብ አሰናበተ፡፡

በሜቲ ኤጀታ (memettiej1@gmail.com) ፍርድ ቤቱ በመ/ር ደስታ ላይ የጥፋተኝነት ብይን በመስጥት ቅጣት ለመወሰን ለዛሬ መጋቢት 5 ቀን 2004 ዓ.ም ቀጥሮ ሰጥቶ ነበር፡፡ የግራ ቀኙን የቅጣት አስተያየት ያዳመጠው የፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቦሌ ምድብ ወንጀል ችሎት መ/ር ደስታ በሰባት ወር … Continue reading

More Galleries | Leave a comment

በዝቋላ ገዳም በቁጥጥር ሥር ውሏል የተባለው ቃጠሎ ዳግመኛ አገርሽቷል!!

አማናዊቷ ደጀ ሰላም!!! ቃጠሎው የገዳሙን ዙሪያ ገባ እያካለለው ነው። የቃጠሎው መንሥኤ “ከሰል አክሳዮች ናቸው” መባሉ አጠራጥሯል። “ትናንት ምሽቱን ነው ዳግመኛ የተቀሰቀሰው፤ የተጠበቀው የአየር እገዛ አልተደረገልንም፤ እሳቱ ዙሪያውን ይዞታል፤ በእሳቱ እየተከበብን፣ በጭሱ እየታፈንን ቢሆንም ባፈር በቅጠሉ እየታገልን ነው፤ ወደ ጠበሉ ከገባ … Continue reading

More Galleries | Leave a comment

የድረሱልን ጥሪ …. ከዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ….. በፍጥነት ወደ መስቀል አደባባይ!!!

ሜቲ ኤጀታ(memettiej1@gmail.com) ለወሬ አልመች ያለው እሳት እንደቀጠለ ነው፡፡ ትናንት በበጎ አድራጊ ምእምናን እና በተወሰኑ የመንግስት አካላት ድጋፍ ጋብ ብሎ የነበረው እሳት ሌሊት ዳግም በመቀስቀሱ ገዳሙ ወደ ታሪክነት ሊቀየር ነው፡፡ ይህን ዜና እያጠናቀርን ባለበት ወቅት ከተለያዩ ማኅበራት እንዲሁም በግላቸው የተውጣጡ ምእመናን … Continue reading

More Galleries | Leave a comment

ዝቋላ ገዳምን በተመለከተ የደጀ ሰላም 2 ዘገባ ዎች

በፖሊስ ጥይት የቆሰሉት ተማሪዎች ሦስት ደርሰዋል ወደ ደብረ ዘይት ለሕክምና ተወስደዋል አጋጣሚው ቃጠሎውን ከመከላከል ሊያዘናጋን አይገባም   በዝቋላ ገዳም የተነሣውን ቃጠሎ ለመከላከል ከተለያዩ አቅጣጫዎች ወደ ስፍራው ከተነቃነቁት አዳማ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች መካከል በፖሊስ ጥይት የቆሰሉት ተማሪዎች ሦስት መሆናቸው ተዘገበ፡፡ በተማሪዎቹ ላይ … Continue reading

More Galleries | Leave a comment

በሰሜን አሜሪካ ምእመናን የዝቋላ አቦ ገዳም በተመለከተ አስቸኳይ ስብሰባ አካሄደዋል::

 >በዋነነት ሶስቱ ማህበራት ተሳትፈዋል        ለስብሰባው መንስኤ በወቅቱ ጉዳይ በተለይም የዝቋላ አቦ ገዳም የእሳት ቃጠሎ የሚታደጉ ወገኖቻችንን ለመርዳት ነው:: ይህ ስብሰባ የተጠራው በፌስ ቡክ እና በስልክ መልእክት በመለዋወጥ ነው:: ስብሰባውም የተካሄደው በኮንፈረንስ ስልክ ነው:: በዋሽንግተን ዲሲ ሠዓት አቆጣጠር 2pm ላይ … Continue reading

More Galleries | Leave a comment

ዛሬ አሰቦት ገዳም አንድ ህፃን ተገደለ

በምዕራብ ሐረርጌ ሜኤሶ ወረዳ በአሰቦት ሥላሴና አባ ሳሙኤል ዘደብረ ወገግ ገዳም የአብነት ተማሪ የሆነው የ7 ዓመቱ ሕፃን ናታን አንበስ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች በ3 ጥይት ተመትቶ መገደሉን የገዳሙ ዋና መጋቢና ምክትል አበምኔት አባ ዘወልደ ማርያም ገለጹ፡፡ ከአባ … Continue reading

More Galleries | Leave a comment